2009-08-14 13:05:27

የመካከለኛይቱ ሪፓብሊካ አፍሪካ


ዩኒሰፍ የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር፣ በመካከለኛይቱ ዴሞክራስያዊት ሬፓብሊክ አገር 700 ሺሕ ሕፃናት በምግብ እጥረት ሳቢያ ለሞት አደጋ ሊጋለጡ እንደሚችሉ በማሳወቅ፣ RealAudioMP3 እነዚህ ካምስት ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑት የክልሉ ሕጻናት ለሞት ያጋልጣል ተብሎ የተፈራለት የርሃብ ችግር እንዲቀረፍ የአለም አቀፍ ማኅበረሰብ እና መንግሥታት ለዚህ ሕዝብ ድጋፍ ለማቅረብ ይራወጡ ዘንድ ማሳሰቡ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ የድርጅቱ መግለጫ በመጥቀስ አስታውቀዋል።

በዚህች አገር ደቡባዊ ክልል የሚኖረው ሕጻን 16% በተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተጠቃ ሲሆን፣ 6.6 ደግሞ እጅግ በጠና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሳቢያ በሞት አፋፋ ላይ እንደሚገኝ የዚህ ሁሉም ችግር መንስኤ ድኽነት መሆኑ ያብራራው የዩኒሰፍ መግለጫ የጠቀሰው የቅድስት መንበር ጋዜጣ በማብራራት 60% ያገሪቱ ሕዝብ እዕለታዊው ኑሮውን በ 1.25 ዶላር እንደሚገፋም ጋዜጣው አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.