2009-08-12 15:25:15

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መልእክት.


በላቲን አመሪካ ኤኳዶር ነጻ የወጣችበት ሁለት መቶኛ ዓመት መዘከርዋ እና ማክበርዋ ከርእሰ ከተማ ኲቶ የደረሰ ዜና አመልክተዋል ። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለኲቶ ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ራውል ኤድዋርዶ ቨላ የደስታ ተለግራም ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እግዚአብሔር በኤኳዶር ህዝብ ላይ ጸጋው እንድያፈስ እንደሚጠልዩ ለኲቶ ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ራውል ኤድዋርዶ ለቫ የላኩት ተለግራም እንደሚያመልክት መግለጫው ገልጠዋል።

የኤኳዶር ክርስትያኖች ፍትሐዊ እና ተባባሪ ኅብረተሰብ እንዲኖር ተግተው እንዲሰሩ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለኲቶ ሊቀ ጳጳስ የላኩት ተሌግራም እንደሚያሳስብ መገለጫው አክሎ መግለጡ የቅድስት መንበር መግለጫ አመልክተዋል።

ከሰው እውቀት ጽንፍ በላይ የሆነ እግዚአብሔር ለኤኳዶር ህዝብ እንዲባርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለኤኳዶር ቤተክርስትያን ባለስልጣን የላኩት የተለግራም መልእክት እንደሚገልጥ መግለጫው አስታውቀዋል።

ኤኳዶር ነጻነትዋ የተጐናጸፈችበት ሁለት መቶኛ ዓመት መሠረት በማድረግ የርእሰ ከተማ ኲቶ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ ራውል ኤድዋርዶ ቨላ ብዙ ህዝብ በተገኘበተ ኲቶ ላይ በሚገኘው ዓቢይ ካተድራል መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ከቦታው የደረሰ ዜና ገልጠዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ፡ ብፁዕ አቡነ ራውል ኤድዋርዶ ቨላ ባሰሙት ስብከታቸው ላይ የሀገሪቱ ጳጳሳት ዝክረ ነጻነት ኤኳዶር ተመርኩሰው ያወጡት ሐዋርያዊ መልእክት በማስታወስ ፡ የሀገሪቱ ፖሊቲካ በሥነ ምግባር ላይ የተመረኰሰ እንዲሆን የፖሊቲካ ሰዎች በዚሁ ረገድ እንዲጓዙ መጠየቃቸው ዜናው ያመለክታል።

ሐቅ ፍትሕ ነጻነት እና ሰላም የሚያረጋግጥ ዲሞክራስያዊ ሥርዓት ለመገንባት የህዝብ ትርታ የሚያዳምጥ ርእዮተ ዓለም መከተል እንደሚያሻ የሀገሪቱ ጳጳሳት ያስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእኽት በአንክሮት እንደሚጠይቅም ተነግረዋል።

የኲቶ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ራውል ኤድዋርዶ ቨላ ቀደም የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ካሪታስ ኢን ቨሪታተ ሐቅ ላይ የተንተራሰች እውነተኛ ፍቅር የተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት አስታውሰው ፡ የዓለም ህዝቦች ለማደግ በጋርዮሽ መስራት እንደሚያሻ የሚመክር እና የሚያስተምር መልእክት በመሆኑ ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች አንብበው እና ተረድተው ገቢራዊ እንድያደርጉት ማሳሰባቸው ይህ ከኲቶ የደረሰ ዜና ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.