2009-08-05 17:13:59

የሩስያ ፓትርያርክ የሰላም ጥሪ


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል የሞስኮ ፓትርያርክ የሩስያና የኡካርያን ሕዝብ ወንድማሞች መሆናቸውን በመግለጽ “ዛሬ ጸሎቴ ወንድማማቾች አንዱ በሌላው ላይ እጅ እንዳያነሳ እንዲሁም ብረት በመማዘዝ በጥላቻ ዓይን እንዳይተያዩ ነው፣ እንደ ደም መፋሰስ ወንድማማቾችን የሚለያይ የለም’’ ሲሉ የሰላም ጥሪ ኣቅርበዋል። ፓትርያርኩ ሁለቱንም አገሮች ማንኛውን ወታደራዊ ግጭት በማውገድ በሰላማዊ መንገድ እንዲተባበሩ ዕድሜ አቅርበዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል ይህን ጥሪ ያቀረቡት ባለፈው እሁድ የቅዱስ ነቢይ ኤልያስ በዓል ለማክበር በሰባስቶፖሊ ከተማ በልዑል ቭላድሚር ካተድራል ብተገኙበት ወቅት መሆኑን ለኦሰርቫቶረ ሮማኖ አመልክተዋል።

ፓትርያርኩ በስብከታቸው ሃገሪቱ መንፈሳዊ አንድነትዋ ኦርቶዶክሳዊ እምነትዋና መንፈሳዊ ዕሴቶችዋ እንድትጠብቅ እግዚኣብሔር ኃይል እንዲሰጣት እንጸልይ፣ ሕዝቦቻችንን ፖሎቲካዊና ብሔራዊ ድምብርን ጥሶ በአንድነት የሚያኖር ኃይል እምነታችን ነው’ በማለት ለሕዝቡ የአንድነትና የሰላም ጥሪ ኣቅርበው ወደ ምዕራባዊ ዩክረይን ለማድረግ አቅደውት የነበረን ጉዞ በጸጥታ ምክንያት አቋርጠው ወደ ሞስኮ ተመለሱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.