2009-08-03 15:40:49

ናይጀሪያ


በናይጀሪያ ታሊባን በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው እስላማዊ ጸንፈኞች እ.ኤ.አ. ሐምሌ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ያቀጣጠሉት ጸረ ክርስትያን አመጽ በጣም አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጠ። እነዚህ ሆኮ ሃራም፣ RealAudioMP3 “ህንጸት/ትምህርት ሓጢኣት ነው” በሚል ዓላማ ታጣቂ ኃይሎች ከናይጀሪያ የጸጥታ ኃይሎች ጋር ያነሳሱት ግጭት ሳቢያ 700 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ሲገለጥ። በናይጀሪይ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የእድገት የፍትህ እና የሰላም ተቋም አስተዳዳሪ ኣባ ኦቢዮራ ኢከ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስትያን እንርዳ ከተሰኘው ያለም አቀፍ የግብረ ሠናይ ማኅበር ጋር ባካሄዱት ውይይት “እነዚህ አክራሪያ ሙስሊሞች ያነሳሱት ግጭት በናይጀሪያ የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ተገደው ሃይማኖታቸውን በመካድ የምስልምና ሃይማኖት እንዲቀበሉ የሚያስገድድ ተግባር ነው” ብለዋል። ይህ በሰሜን ያናጀሪያ ክልል ከባለፈው ሐምሌ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. አክራሪያን ሙስሊሞች ያነሳሱት ግጭት በናይጀሪያ የእስላም ሃይማኖት ሕግ እርሱም ሻሪአ የአገሪቱ ብሔራዊ የመስተዳደሪያ ደንብ ይሆን ዘንድ አልሞ የተጀመረ ጥቃት መሆኑ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.