2009-07-31 14:27:02

የሩሲያና የኡክራይን ግኑኝነት መሠረት


የሞስኮና የመላዋ ሩሲያ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል በዚህ ሶስተኛ ቀኑን በያዘው የኡክራይን ጉብኝታቸው ዕለት በሩሲያና በኡክራይን መካከል ያለው ግኑኝነት RealAudioMP3 በፖለቲካዊ ንድፈ ሀሳብ ላይ የጸና ሳይሆን በክርስቶስ አንድነት ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል። ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል የኡክራይን ጉብኝታቸውን በኪየቭ የሚከበረ በኡክራይን የኦርቶዶክስ እምነት እንዲስፋፋ ያደረገው የቅዱስ ቭላድሚሮ ዓመታዊ ክብረ በዓል ጋር የተዛመደ መሆኑ ሲገለጥ፣ ለበዓሉ ምክንያት ያረገው መስዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የሞስኮ ፓትሪያርካዊት የኡክራይን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ መሆናቸውም ተገልጠዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል በሩሲያና በኡክራይን መካከል ያለው ወዳጅነት እና የወንድማማችነት መንፈስ በእምነት ላይ የጸና መሆኑ እና ዛሬም ህያው መሆኑ ቀርቤ ለማረጋገጥ ችያለሁ ማለታቸውም ሎሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ትላንትና ባወጣው ኅትመቱ አመልክቶታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.