Home Archivio
2009-07-29 13:33:37
አፍጋኒስታን
ባፍካኒስታን ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የርእሰ ብሔር ምርጫ ሊረጋገጥ ሶስት ሳምንት ቀርቶት ባለበት በአሁኑ ሰዓት በአገሪቱ አመጽ እጅግ እያንሰራፋ መምጣቱ ተገልጠዋል። ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ስምንት የአገሪቱ
የጸጥታ ኃይል አባልት በሄልማድ አውራጃ ይጓዙባት የነበረቸው መኪና በደረሰባት የተቀበረ ቦምብ ፍንዳታ ሳቢያ ለሞት መዳረጋቸው ተገልጠ። የታሌባን ታጣቂ ህይሎች በገፍ የመሸጉበት ሥፍራ ነው ተብሎ በሚነገርለት ባፍጋኒስታን ደቡባዊው ክልል የተባበሩት ያሜሪካ መንግሥታት የመከላከያ ኃይል አባላት እና የታላቋ ብሪታኒያ የመከላከያ ኃይል አባላት ሰፊ ጥቃት እየሰነዘሩ መሆናቸው ይንገራል። አገሪቱ እንዲህ ባለ ከፍተኛ ውጥረት ታምሳ ባለችበት ሁኔታ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
በዚህ በሚካሄደው ምርጫ እ.ኤ.አ. በ 2004 ዓ.ም. በተካሄደው የሕዝባዊ ምርጫ በማሸነፍ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ለመሆን የበቁት ዳግም ለምርጫ የቀረቡት ርእሰ ብሔር ሃሚድ ካርዛይ የማሸነፍ እድል አላቸው ይባላል።
በጠቅላላ ስለ ወቅታዊው ያፍጋኒስታን ሁኔታ በማስመከት ባፍጋኒስታን በዳግም ግንባታ እና በግብረ ሰናይ እቅዶች ለተሰማራው ፓንገአ በመባል ለሚጠራው መንግሥታዊ ያለሆነው የግብረ ሰናይ ማኅበር ተጠሪ ሲሞና ላዞኒ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ባፍጋኒስታን ሙስና እጅግ በሁሉም የመንግሥትም ይሁን የግልና ሕዝባውያን ዘርፎች ዘንድ የተስፋፋ መሆኑ እና በሌላው ረገድ ደግሞ የወንጀል ቡድኖች ከጦር ጌቶች ድጋፍ በማግኘት የተዋቀረ የወንጀል ድርጅት ሆነው አገሪቱን ለአቢይ ችግር ያጋለጡ መሆናቸው ገልጠው። የሚካሄደው ምርጫ በነዚህ ሁለት ችግሮች የሚሸኘው ሕዝባዊ ምርጫ በመሆኑም ረገድ ነጻ ይሆናል ብሎ ለመናገር ያዳግታል ብለዋል።
የተባበሩት ያሜሪካ መንግሥታት ዋና ጸሃፊ ሂላሪ ክሊንተን እና የታላቋ ብሪጣኒያ አቻቸው ዳቪድ ሚሊባንድ ያአገሪቱ ሁኔታ እግምት ውስጥ በማስገባት እና በወቅታዊው ያገሪቱ ሁኔታ አስገዳጅ መሠረት፣ በአፍጋኒስታ በሚካሄደው ህዝባዊ ምርጫ ለዘብተኛ አመለካከት ያላቸው ታሌባኖች የመሳተፍ እድል ይኖራቸው ዘንድ የመንግሥቶቻቸው ውሳኔ እግብር ላይ እንዲውል ጥረት እያደረጉ መሆናቸም ላዞኒ አብራርተው ይህ አይነቱ ውሳኔ ቀድሞ እግብር ላይ መዋል ነበረበት ብለዋል።
እጩ ተመራጮች የወቅቱ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ሃሚድ ካርዛይ፣ ለካርዛይ መንግሥት ሚኒስትሮች በመሆን ያገለገሉት አብዱላህ አብዱላህ፣ አሽራፍ ጋኒ እና ራምዛን ሃሻርዶስት እንደሚገኙበትም ገልጠው፣ በነዚህ ተመራጮች ዘንድ በሚገኘው የምርጫው ውጤት አማካኝነት ግጭትም ይሁን ውጥረት እንደማይኖር ግልጽ ቢሆንም ቅሉ ሌሎች 41 እጩ ተመራጮች ግን የሚገኘው የምርጫው ውጤት መሠረት ችግር ሊፈጥሩ እንደሚችሉም ይጠረጠራል።
All the contents on this site are copyrighted ©.