2009-07-29 13:34:47

አለ ድንበር የዓለም አቀፍ የሓኪሞች የግብረ ሰናይ ማኅበር


የሕገ ወጥ ስደተኞች ወደ ኤውሮጳ የሚያደርጉት ጸዓት አሁንም እየቀጠለ መሆኑ ሲነገር፣ ማልታ በሚገኘው በስደተኞች ጊዚያዊ መጠለያ ያሉት ስደተኞች ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው እንደሚግኙ አለ ድንበር የዓለም አቀፍ የሓኪሞች ማኅበር አስታውቀዋል። RealAudioMP3

ማልታ በሚገኘው መጠለያ ሠፈር የስደተኞች መብት እና ፈቃድ እንደሚጣስ ያስታወቀው ይህ የሓኪሞች ማኅበር በማሳሰብ፣ ስለ ሁኔታው በማልታ የማኅበሩ ቅርንጫፍ ተጠሪ ቸቺሊያ ሰፒያ፣ በማልታ ሶስት የስደተኞች መጠለያ ሠፈር እንደሚገኙና በመጠለያው ሠፈር ያለው የሰደተኛው አያያዝ ኢሰብአዊነት የተሞላው፣ መሠረታዊ የጤና ጥበቃ አገልግሎት የማይሰጥበትም ጭምር መሆኑ ገልጠው፣ የጤና መታወክ ያለውም የሌለውም ወንዱም ሴቱም ሕጻኑም ሁሉ ባንድ ላይ የሚያዝበት በመሆኑ የመጠለያው ሠፈር ሁኔታ የስደተኛው ችግር እያባባሰው ነው ብለዋል።

የስደተኛው ችግር ቀርቦ በማጤን የሓኪሞች ማኅበር ከማልታ መንግሥት እና የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተሉት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በመወያየት የስደተኛው መብትና ፈቃድ እንዲከበር ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል።

መንግሥታት ስደተኛው ወደ መጣበት ለመሸኘት ከመራወጥ ይልቅ፣ በቅድሚያ ስደተኛው ከየት አገር እንደመጣ ማጣራት፣ ስደተኛው የመጣበት አገር ወቅታዊ ሁኔታ ቀድሞ ማወቅ የስደተኛው ለስደት የዳረጉት ምክንያቶች ለይቶ ለማወቅ ቀርቦ አንድ በአንድ ማዳመጥ ወሳኝ ነው፣ ያለም አቀፍ የመብት እና ፈቃድ ውሳኔ የሚያመለክተው ሂደትም ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.