2009-07-27 13:48:33

የላይበሪያ ብፁዓን ጳጳሳት የእውነትና የእርቅ ድርገት መገልጫ


የላይበሪያ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ እ.ፈ.አ. ከ 1989 ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም. በአገራቸው ተካሂዶ በነበረው የርስ በርስ ጦርነት ወቅት የተፈጸመው እልቂት፣ ዘር ማጥፋት የጦር ወንጀል በማጣራት ሓቅ RealAudioMP3 ገሃድ ወጥቶ በሓቅ ላይ የጸና እርቅ እንዲረጋገጥ ጥረት የሚያደርገው የሓቅና የእርቅ ድርገት ያጠናቀረወ ሰነድ ባለፈው ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ይፋ ማድረጉ ተገለጠ።

ይህ የአንድ ዓመት የፈጀው ልዩ ምርመራ እና ጥናት አማካኝነት የብፁዓን ጳጳሳት ድርገት ያጠናቀረው ሰነድ ከአገሪቱ የተለያዩ የፖለቲካ አካላት አሉታዊ እና አወንታዊ አስተያየት እየተሰጠበት መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

የላይበሪያ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ፣ የጉባኤው ድርገት ያጠናቀረው ሰነድ ለአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት የሚበጅ መሆኑ አስተያየት በመስጠት፣ አንዳንድ የፖለቲካ አካላት ሰነዱን በማስደገፍ እየሰጡት ያለው አሉታዊ አስተያየት ችላ የማይባል አሳሳቢ መሆኑ ገልጠዋል። በሓቅ ላይ ያልጸና እርቅ ዘለቄታ የሌለው ቀኑ ጠብቆ የብቀላው መንፈስ ሆኖ ብቅ እንዲል የሚገፋፋው እምቅ ኋይል ስለ ሚሆንም፣ የዚህ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትሕና ሰላም ድርገት በማብራራት ሰነዱ ለአገር እና ለሕዝብ ጥቅም የሚበጅ ነው በማለት አስተያየት ሰጥቶበታል። ሰላም የሚረጋገጠው በውይይት እንጂ ኃይል በመጠቀም እንዳልሆነ ይህ የላይበሪይ የእርስ በርስ ግጭት ጉዳይ እንዲያጣራ እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም. የተመለመለው የላይበሪያ የብፁዓን ጳጳሳት የሓቅና ዕርቅ ድርገት ባወጣው ሰነድ አመልክተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.