2009-07-24 13:42:44

ፍቅር በሐቅ


እዚህ ሮማ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ የጉባኤ አዳራሽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሓቅ በሚል ርእስ ሥር የደረስዋት አዋዲት መልእክት ማእክለ ያደረገ የኤኮኖሚ ሊቃውንት ምሁራን እና የመንግሥት ተጠሪዎች RealAudioMP3 የተሳተፉበት አውደ ጥናት መካሄዱ ሲገለጥ፣ በዚህ በተካሄደው አውደ ጥናት የተገኙት እና ንግግር ያሰሙት ጳጳሳዊ የላተራነንሰስ መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ እና የጳጳሳዊ የሕይወት ተቋም ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ እና የኢጣሊያ የኤኮኖሚ ሚኒስትር ጁሉዮ ትረሞንቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊሲኬላ “ይላሉ የቀዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዋዲት መልእክት ትእዛዝ ሳይሆን ትክክለኛ የኤኮኖሚ እና የእድገት ትርጉም የምታስረዳ ነች ብለዋል።

ደንብ ያለው በሥነ ምግባርና ግብረ ገብ የተካነ ኤኮኖሚ የምታነቃቃ እና ትርፍ ሳይሆን በቅድሚያ ሰውን ማእክል ያደረገ መሆን እንደሚገባ የምታስተምር ተገቢ ትርፍ ማግኘት ተገቢ መሆን የምታሳስብ ነች፣ ስለዚህ ኤኮኖሚ የሙያ/የቴክኒክ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሰውን የሚመለከት መሆኑ መዘንጋት እንደሌለበት ትብብርና መደጋገፍን ወሳኝ መሆኑ የምታስገነዝብ ነች ብለዋል።

የኢጣሊያው የኤኮኖሚ ሚኒ. ጁሊዮ ትረሞንቲ የር.ሊ.ጳ አዋዲት መልእክት ወቅታዊውን ዓለም የምትዳስስ የጋራ ጥቅም ማእክል መሆን እንደሚገባው የምታስተምር ለኤኮኖሚ ለእድገት መሠረት ነች ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.