2009-07-24 13:40:11

የሰብአዊ መብትና ፈቃድ መከበር


የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በጠና በሰብአዊ መብት እና ፈቃድ RealAudioMP3 አመጽ ተጋልጠው ለሚገኙት ድጋፉን እና ከለላ ይሆንም ዘንድ በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ቸለስቲኖ ሚሊዮረ ትላትና ተጀምሮ ዛሬ በሚጠቃለለው በዚህ የአለም አቀፍ ድርጅት የሰብአዊ መብትና ፈቅድ ጥበቃ በሚልር ርእሰ ጉዳይ RealAudioMP3 በመካሄድ ላይ ስላለው ጉባኤ አስመልክተው ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመጥቀስ፣ በጆርጂያ፣ በኦሰዚያ በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ በስሪላንካ እና በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የሚታየው የሰብአዊ መብት ረገጣ ለማንም የተሰወረ እንዳልሆነም በማስታወስ ያለም አቀፍ ማኅበረሰብ በመብትና ፈቃድ ረገጣ የሚሰቃየው ሕዝብ መከላከል ተቀዳሚ ዓላማው ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።

በአንዳንድ የኤውሮጳ አገሮች የኮሙኒዝም ሥርዓት ይከተሉ የነበሩት መንግሥታት እየተገለሉ በመምጣታቸው ምክንያት፣ ቅድሚያ ይሰጠው የነበረው የመሬት አቀማመጥ ፖሊቲካ ሥልት ወድቅ እይሆነ በግል እና በማህበረሰብ ላይ ትኵረት እየተሰጠው ያለው የሰብአዊ መብት ጉዳይ ማእከል ያደረገ የጸጥታና ደህንነት እቅድ ገቢራዊ መሆን እንደጀመረም አስታውሰው፣ ማንም ሕዝብ ጦርነት በሚካሄድበት ክልል ቢሆንም’ኳ የመብትና ፈቃድ ረገጣ ኢላማ መሆን የለበትም፣ ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ሰውን ማእከል ያደረገ ፖለቲካ እውን መሆን አለበት፣ በስነ ሓሳብ አማካኝነት ጸንቶ የነበረው የልዩነት አጥር ተወግዶ ይኸንን ተከትሎ የተከሰተው ለውጥ የሰብአዊ መብትና ፈቃድ መከበር ያነቃቃ ቢሆንም ቅል በጸጥታና ደህንነት ሰበብ የሚታየው የመብት እና የፈቃድ ረገጣ ጨርሶ ማስወገድ የመንግሥታት ተቀዳሚ ውሳኔ መሆን ይገባዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.