2009-07-24 15:57:56

ሰብአዊ ቀውሶች ዓለም አቀፋዊ መፍትሔ ይሻሉ አቡነ ቶማሲ .


በስዊትጸርላንድ ጀነቭ ላይ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ በድርጅቶቹ የኤኮኖሚ እና ማኅበራዊ ምክር ቤት ያካሄደው ስብሰባ መሳተፋቸው ከቦታው የደረሰ ዜና ይገልጣል።

ምክር ቤቱ በዓለም ዙርያ የሲቪል ህዝቦች መብቶች ሲጣሱ እና የግጭቶች ሰለባ ሲሆኑ፡ የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብቶች አክባሪ ድርጅት ሚና እና ሐላፊነት ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱ ከጀነቭ የመጣ ዜና ገልጠዋል።

በአሁኑ ወቅት አስር ሚልዮን ህዝብ አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ሕጻናት በየስደተኞች ሰፈሮች እንደሚኖሩ ሀገራቸው ውስጥ እና ውጭ የተፈናቀሉ ደግሞ ከሀያ ስድስት ሚልዮን እንደማያንሱ በጀነቭ የተበበሩ መንግስታት ተቋሞች የቅድስት መንበር ወኪል ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ ለምክር ቤቱ መግለጣቸው ዜናው አምልክተዋል።

በርካታ ቤተ ሰቦች እና ማኅበረሰ ቦች ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ መሆናቸው በሰነድ ደግፈው ለምክር ቤቱ የገለጡት ሐዋርያዊ ወኪሉ ፡ የተባበሩት መንግስታት የሰው መብት ኮሚሽን ለዚህ አስከፊ ያሉት ችግር ዘላቂ መፍትሔ እንድያፈላልግ መጠየቃቸው ተነግረዋል።

የዓለም ሰብአዊ ቀውሶች ዓለም አቀፋዊ መፍትሔ ያሻቸዋል ያሉት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ መፍትሔው አስቸኳይ ትክክለኛ እና ዘላቂ እንዲሆን ማሳሰባቸው አብሮ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

በተለያዩ ሀገራት በተለይ በታዳጊዎቹ ግጭት በተነሳ ቁጥር ሰላማውያን ሰዎች ሰለባ ሲሆኑ እንደሚታዩ በጀነቭ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል መግለጠቸው ተመልክተዋል።

ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የነዚህ ሰዎች የሕትወት ዋስትና ለመስጠት ዓለም አቀፍ ስትራተጂ መቀየስ እንደሚገባው ወኪሉ መናገራቸውም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.