2009-07-24 15:57:08

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በየበጋ ዕረፍት ላይ ይገኛሉ.


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በሰሜናዊ ኢጣልያ ቻለት ዲ ለስ ኮምበስ በተባለ ቦታ ዕረፍት ላይ እንደሚገኙ የሚታወስ ነው ።

የዕረፍት ግዝያቸው በጸሎት እና አስተንትኖ እንዲሁም ከየክልሉ ህዝቦች ጋር በመገናኘት እና የመዝናናት ግዜ እንዳላቸው የተጠሰ ሲሆን ግዝታቸው በሰላማዊ አኳሃን እያሳለፉትመሆናቸው የቫቲካን ምገናኛ ብዙኀን ገልጠዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ አከባቢ ከሚኖር ህዝብ በየግዜው እንደሚገናኙ እና አንዳንድ እንግዶችም እየተቀበሉ ሰላማዊ የዕረፍት ግዜ እያሳለፉ መሆናቸው የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከቦታው ገልጠዋል።

ቃል አቀባዩ በሰጡት መግለጫ መሠረት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ዛሬ ከቀትር በኃላ አ ኦስታ ውስጥ በሚገኘው ካተድራል በርካታ ምእምነናን በተገኙበት ጸሎተ ሰርክ መርተው ደግመዋል ።

ይህ በዚህ እንዳለ ከአንድ ሳምንት በፊት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወድቀው ክንዳቸው ላይ መቁሰልት እንደደረሰባቸው የሚታወስ ሲሆን ፡ ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው በየቫቲካን እና የቫል ዳ ኦስታ ሀኪሞች የሕክምና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስታውቀዋል ።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ቤተክርስትያን ነክ ጉዳዮች ሰነዶች ይዘው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሚገኙበት የዕረፍት ቦታ መድረሳቸው ቃል አቀባዩ በተጨማሪ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.