2009-07-24 13:38:45

ር.ሊ.ጳ. ለቀድሞ የፊሊፒንስ ርእሰ ብሔር ኮራዞን አኩይኖ መልእክት አስተላለፉ


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በፊሊፒንስ ርእሰ ከተማ ማኒላ በሚገኘው ሆስፒታል ባጋጠማቸው የነቀርሳ በሽታ ምክንያት በሕክምና ላይ ለሚገኙት ለቀድሞ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ኮራዞን RealAudioMP3 አኵይኖ ተሎ መዳንን ተመኝተው፣ በጸሎታቸው እንደሚያስታውሷዋቸውም የሚረጋገጥ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብጹዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ፊርማ የሰፈረበት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።

እኚህ 76 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የፊሊፒንስ የቀድሞ ርእሰ ብሔር አኵይኖ የር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 መልእክት እንደደረሳቸው ደስ መሰኘታቸ እና እጅግ መጽናናታቸው ገልጠዋል። ኮራዞን አኵይኖ እ.ኤ.አ. ከ 1986 ዓ.ም. እስከ 1992 ዓ.ም. የፊሊፒንስ የመጀመርያ ሴት መሪ እና ባገሪቱ የዲሞክራሲው ሥርዓት እንዲረጋገጥ ፈር ያስያዙ በሁሉም የሚዘከር ናቸው።








All the contents on this site are copyrighted ©.