2009-07-24 13:45:16

ማላዊ


ባለፈው ሓምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. የማላዊ ካቶሊክ ቤተክርስትያን አራት የተለያዩ በዓላት ማክበሯ ተገለጠ። የብላንትረ ሰበካ 50ኛው ዓመት ምሥረታ፣ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በማላዊ ሓዋርያዊ ጉብኝት RealAudioMP3 ያካሄዱበት 20ኛ ዓመት፣ የቅዱስ ጳውሎስ ዓመተ እዮቤል መዝጊያ በዚያ እለትም ሶስት ዲያቆናት ማዕርገ ክህነት መቀበላል ሌላ ተጨማሪ በዓል ሲሆን።

ፊደስ የዜና አገልግሎት እንዳሳወቀው አራቱን በዓላት በክልሉ ቤተ ክርስያን እና ምእመናን ደምቆ መከበሩ ሲነገር፣ በበዓሉ 8 ብፁዓን ጳጳሳት በዛምቢያ እና በማላዊ ለቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ጂራሶሊ ጭምር መሳተፋቸው የዜና አገልግሎቱ አስታውቀዋል። የር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የማላዊ ሓዋርያዊ ጉብኝት ባገሪቱ እምነትን ዳግም መኖር ፍላጎት እና የማላዊ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ወንጌልን በሕይወት መኖር እና ኅሊናን ያነቃቃ ክርስትያን የመህን ጥሪ ዳግም እንዲጨበጥ ማድረጉ ላይ ባተኮረ ጥልቅ ስሜት ተዘክረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.