2009-07-22 13:01:40

የካቶሊክ ባህል ጠልቆና ጠንቅቆ ለማወቅ


ካቶሊክና አንግሊካዊት አቢያተ ክርስትያን ያንድ ሜዳሊያ ሁለት ገጾች በሚል ርእስ የካንተርበርይ እና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን አንድነት የበላይ መሪ ሊቀ ጳጳሳት ርዋን ዊሊያምስ “ካቶሊካዊነትን ማረጋገጥ RealAudioMP3 ” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው አንግሊካዊ እንቅስቃሴ ባነቃቃው ስብሰባ ተገኝተው ንግግር ማሰማታቸው ተገልጠዋል። የዚህ እ.ኤ.አ. በ 1991 ዓ.ም. ምእመናን ስለ ካቶሊክ ባህል ለማወቅ የሚያነቃቃው ያንግሊካውያን እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ጆናታን ክላርክ እና መጋቢ አንጀላ ቲልባይ በጋራ ያነቃቃቱ ስብሰባ መሆኑም ሲገለጥ፣ ብዙ ያንግሊካውያን ምእመናን ስለ ካቶሊክ ባህልና ሥርዓት ለማወቅ አቢይ ፍላጎት እንዳላቸው ክላርክ በተካሄደው ስብሰባ ማሳወቃቸውም ሎሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰኘው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትና ኅትመቱ አስታውቀዋል።

ስለ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ቲዮሎጊያ፣ ቅዱሳት ሚስጥራት፣ መሪ ትህርቶች ስለ ተአምኖተ ሃይማኖት ጭምር ለማወቅ ያንግሊካው ውህደት ሊቃነ ጳጳሳት ቄሶች እና ምእመናን ያላቸው ፍላጎት ከፍ እያለ መምጣቱ ያረጋገጠው ካቶሊካውነትን ማረጋገጥ የተሰኘው ያንግሊካውያን ምእመናን እንቅስቃሴ የእምነታቸው መሠረት የሆነውን ባህል በማወቅ ላይ እያደጉ መሆናቸው ክላርክ ማብራራታቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አሳወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.