2009-07-22 12:58:54

የምዕራብ አፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት


“በምዕራብ አፍሪካ አገሮች የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲስፋፋ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል እንዲሁም የክርስትያኖች አንድነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ውይይት ያለው ሚና” በሚል ርእስ ሥር ናይጀሪያ ጋና ሰራሊዮን ላይበሪያና ጋምቢያ RealAudioMP3 የሚያቅፈው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ማኅበር በተለያዩ ሃይማኖቶች እና እንዲሁም ለክርስትያኖች አንድነት መረጋገጥ የሚደረገውን ውይይት በሚከታተሉት ድርገቶቻቸው አማካኝነት በጋና ርእሰ ከተማ አክራ መካሄዱ ተገለጠ።

እ.ኤ.አ. ይህ ከሐምሌ 13 ቀን እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. የተካሄደው ስብሰባ ባወጣው የጋራመግለጫ ዴሞክራሲ የልማት መሠረት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሃይማኖቱ እና ፖለቲካዊ አመለካከቱ ተከብሮለት በጋራ ላገር ጥቅም እና ብልጽግና በማተኮር በመተባበር እና በመደጋገፍ ለመኖር የሚያግዝ ሥርዓት መሰረት መሆኑ ተመልክቷል።

በምዕራብ አፍሪካ ክልል አገሮች የሚታየው የዴሞክራሲው ሥርዓት ሙሉ በሙሉ የሕዝብ ተሳትፎ የተረጋገጠበት ነው ብሎ ለመናገር እንደሚያዳግት እና በተለይ ደግሞ የፖሊቲካ ብሔራዊ ምርጫዎች ማጭበርበር የሚታይበት መሆኑ የጋራው መግለጫ በማመልከት በዚህ ክልል የፖለቲካ ሰልፎች እና አንዳንድ ሃይማኖቶች ድኽነት መሃይምነት ፍትሕ አልቦነት የመሳሰሉት በስፋት የሚታዩት ዓበይት ችግሮች ተገን በማድረግ የሕዝቡን ችግር እንደሚያባብሱ የተካሄደው ስብሰባ መገልጫ ይጠቁማል።

በመጨረሻም ትክክለኛ እና የተሟላ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ሕንጸት ለዜጎች በማቅረብ ሕዝቡ የአገሩ ጉዳይ ችላ እንዳይል መብቱና ፈቃዱ ተጠብቆለት ሃላፊነት እና አገር ወዳድነት አጣምሮ ለመኖር እንዲችል ተገቢ ድጋፍ እና ሕንጸት ማግኘት እንደሚገባው የጋራው መገልጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.