Home Archivio
2009-07-20 14:07:49
ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ
በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ ርእሰ ከተማ ኪንሻሳ የሚገኙት የካቶሊክ ተቋሞች ባንድ ላይ በመጠራነፍ የኮንጎ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ ለመሆን መብቃታቸው ተገለጠ። የአገሪቱ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር
የተቋቋመው የኮንጎ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ የሹምቤ ሊቀ ጳጵሳት ብፁዕ ኣቡነ ኒኮላስ ድጆሞ ሎላ የተቋቋመው መንበረ ጥበብ እቅድ በተለያዩ ዘፈሮች ዜጎችን በማነጽ የሕዝብ እና የአገር ጥቅም የሚያስቀድሙ ለህዝብ ጥቅም የሚያገለግሉ ብቃት ያላቸው ምሁራን በማዘጋጀት የሃገር እና የቤተክርስትያን እድገት ለማነቃቃት የሚል መሆኑ በመግለጥ፣ መንበረ ጥበቡ ከሚያካታቸው የትምህርት ዘርፎች ውስጥ ቲዮሎጊያ፣ ፍልስፍና፣ የኤኮኖሚና የስነ እድገት፣ የስነ መገናኛ ብዙኃን፣ የስነ ፖለቲካ እና የቤተ ክርስትያን ቀኖና የሚሉትን ያካተተም ጭምር መሆኑ ጠቅሰው፣ መንበረ ጥበቡ 2.200 ተማሪዎች 77 አስተማሪዎች 20 ረዳት አስተማሪዎች 63 የመንበረ ጥበቡ የመስተዳድር እና ያገልግሎት መስጫ ሠራተኞች እንዳሉትም ገልጠዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.