2009-07-16 08:44:17

ያፍሪካ ልኡካን ማኅበር


ያፍሪካ ልኡካን በሚል መጠሪያ የሚታወቁት ባድሪ ቢያንኪ ማኅበር በኡጋንዳ ወንጌል ለማበሠር የገቡበትን 150ኛው ዓመት ተዘክረዋል። 150ኛውን ዓመት ለመዘከር ባለፈው እሁድ ፓድሪ ቢያንኪ ማኅበር ለመጀመሪያ ጊዜ RealAudioMP3 በኡጋንዳ በደረሱባት ቡጋንዳ የወቅቱ ብካሱቢ ከተማ መሥዋዕተ ቅዳሴ መቅረቡ ቺሳ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ አባ ሩዲ ለሄነርትዝ “ማኅበሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ኡጋንዳ ሲገባ በኤውሮጳ በተለያዩ የልኡካን ማኅበራት ዘንድ የነበረው የመከፋፈል የእኔ ባይነት መንፈስ የፈጠረው ችግርም አብሮት እደተጓዘ አስታውሰው፣ የዚህ አይነት የመከፋፋል ፈተና ዛሬም በዚህች አገር እንደሚታይ አስታውሰው፣ የተፎካካሪነት መንፈስ የቀሰቀሰው መከፋፈል ባፍሪካ ያስከተለው ችግር ለማንም የማይሰወር የታሪክ ሓቅ ነው” እንዳሉም ቺሳ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የእራስ ባህል የበለጠ የጠራ አድርጎት ግምት በመስጠት እና በዚህ አኳያ የተመራ የልኡካነ ወንጌል ሓዋርያዊ ኖልዎ በተለያዩ ያፍሪካ አገሮች ያስከተለው ውጥረት አመጽ ያስታወሱት አባ ለሄነርትዝ በማኅብሩ ስም ያፍሪካን ባህል ዝቅ አድርገው የፈረዱ አፍሪካውያንን የሚያንቋሽሹ ባፍሪካ የተፈጸመው በደልና ግፍ በመዘርዘር ላፍሪካ ይቅርታን ጠይቀዋል።

በተካሄደው በዓል የካምፓላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካሪዲናል ኤማኑኤል ዋማላ በኡጋንዳ ወንጌልን ለማብሰር የተላኩት የፓድሪ ቢያንኪ ማኅበር አባላትን አስታውሰው በተለይ ደግሞ ካፍሪካ ባህል ጋር ተግባብተው የእራሳቸው በማድረግ አፍሪካውያን በመሆን በዚህች አገር ወንጌልን ያበሰሩ ቀደምት የማኅበሩ ልኡካን ኣባ ሲመኦን ሎርደል እና ወንድም ዴልማስ አማንስ የፈረንሳይ ዜጎችን አስታውሰው እነዚህ ሁለቱ አበይት ቀደምት የፓድሪ ቢያንካ ልኡካን የቅድስና አዋጅ ሂደት በቤተ ክርስትያን እንዲጀመርላቸው አባ ለሄነርትዝ ያቀረቡት ሐሳብ እንደሚደገፍት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.