2009-07-14 16:59:34

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የፕረሰዳንት ባራክ ኦባማ ግኑኝነት.


ባለፈው ዓርብ ከቀትር በኃላ በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛና እና የተባበሩት መንግስታት አመሪካ መንግስት መሪ በፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ መካከል የተካሄደው የመጀመርያ ግኑኝነት ሰላም እድገት እና የሕይወት ጥበቃ ትኩረት የሰጠ መኖሩ ቫቲካን ያወጣው መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚሁ መግለጫ መሠረት ሁለቱ ባለስልጥናት ከዚህ ባሻገር ርእሰ ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ እና የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ እና የውስጠ ሃይማኖቶች ውይይት ፡ በተመልከቱ ርእሰ ጉዳዮች ሐሳብ ለሓሳብ ተለዋውጠዋል።

የተባበሩት መንግስታት አመሪካ መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጋር ለመገናኘት ዕድል በማግኘታቸው ትልቅ ክብር እንደተሰማቸው መግለጣቸው ያመለከተ የቫቲካን መግለጫ ፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመካከለኛው ጣልያን የተካሄደው የቡድን ስምንት በኢንዱስትሪ የበለጠጉ ሃገራት የመሪዎች ጉባኤ ውጤት በተመለከተ ፕረሲዳንቱን መጠየቃቸው እና ፕረሲዳንቱ ጉባኤው ስኬታማ መኖሩ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መግለጣቸው መግለጫው አክሎ አመልክተዋል።

የቫቲካን መግለጫ እንደገለጠው የቅዱስ አባታች ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የተባበሩት መንግስታት አመሪካ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ በየቅድስነታቸው የግል ጽሕፈት ቤት ውስጥ ከአርባ ደቂቃዎች ለበለጠ ግዜ መነጋገራቸው ጥቁሞ ፡ ዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ለአፍሪቃ እና ለላቲን አመሪካ ሀገራት የሚሰጠው የልማት ርዳታዎች አንስተው ተወያይተውል።

ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ከየቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ከብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ጋር መወያየታቸውም መግለቻው አስታውሰዋል።

ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ስጦታዎች እንደተለዋወወጡ መለዋወጡመግለጨው አመልክተዋል።

መግለጫው እንዳመለከተው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለፕረሲዳንቱ በቅርቡ ለኅትመት እና ንባብ የበቃው ለአለም ያስተላለፉት “Caritas in veritate እውነተኛይቱ ፍቅር ሐቅ ላይ የተመረኰሰች ናት “የተሰየመችው ሐዋርያዊ መልእክት ለፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ስጦታ ሲሰጡዋቸው ፕረሲዳንቱም ለርእሰ ሊቃነ ጳጳጳሳት ከ1988 እስከ 2007 እኤአ በየብፁዕ አቡነ ጆን ኒው ማን ቅሪት ላይ የነበረው አክሚም ለቅድስነታቸው አበርክተዋል።

የአመሪካ ዜጋ ብፁዕ አቡነ ጆን ኒው ማን የሀገሪቱ የመጀመርያ ጳጳስ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡ በዚሁ መግለጫ መሠረት ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ በተባበሩት መንግስታት በጠና ታመሙ የሚገኙ ሰነተር ተድ ኬነዲ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጻፉት የግል መልእክት አስረክበዋል።

የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የተባበሩት መንግስታት አመሪካ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ግኑኝነት በተመለከተ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስተያየት ሲሰጡ፡ ሁለቱ ባለስልጣናት በዚሁ የመጀመርያ ግዜ ግንኙነታቸው ዓለም አቀፍ እና ግብረ ገብነት ነክ ጉዳዮች ለምሳሌ ጽንስ ማስወረድ በተመለከተ ሐሳብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል።

በመሠረቱ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ግንኙነት ስኬታማ እና አዎንታዊ ነበር ያሉት የቫቲካ ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ስለ ዘር ሕይወት ያላትን ሐሳብ እና አቋም ለፕረሲዳንቱ ገልጠውላቸዋል።

የተባበሩት መንግስታት አመሪካ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ዓለማችን ፊት የተደቀኑ አበይት ችግሮች ለመቅረፍ ዝግጁነት ማሳየታቸው ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎማባርዲ ጠቅሰው ፡ ፕረሲዳንቱ የሚደነቁ መሆናቸውም አመለክተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ፡ በቫቲካን የCnn እና የብሔራዊ ካቶሊክ ጋዜጣ ዘጋቢ ጆን አለን እንዳመለከቱት፡ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፊት ጽንስ የማስወረድ ተግባር ለመቀነስ ቃል በመግባታቸው ሥነ ምግባራዊ ሐላፈነት መውሰዳቸው ያመለክታል።

ይሁን እንጂ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ጽንስ ማስወረድ ለመቀነስ ያላቸው እቅድ ለአመሪካ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን እና ለሕይወት ጥበቃ ለቆሙት የሀገሪቱ ድርጅቶች በቂ መሆኑ በእጅጉ እንደሚያጠራጥር ጆን አለን ገልጠዋል።

የሰው ዘር ሕይወት ጥበቃ በተመለከተ በየአመሪካ ቤተክርስትያን እና መንግስት መካከል ያለው ልዩነት በቀላሉ የሚወገድ መስሎ እንደማይታይ ጆን አለን በተጨማሪ ማመልከተታቸው ተገልጠዋል።

በቫቲካን የCnn እና የብሔራዊ ካቶሊክ ጋዜጣ ዘጋቢ በጆን አለን አስተያየት ፡ በቤተክርስትያን እና በአመሪካ መንግስት ጽንስ ማስወረድ እና የሽል ስቲም ሴል በተመለከተ ልዩነቶች ይኑሩ እንጂ በዚሁ ጉጋይ በሀለቱ ወገኖች መካከል ቀጣይ ውይይት እንደሚካሄድ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ጉዳይ ተባብረው ለመስራት የሚያስችላቸው መለካም ሁኔታ እንዳለ ግን ጥርጥር የለም።








All the contents on this site are copyrighted ©.