2009-07-11 08:23:05

የተለያዩ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አስተያየት


ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “ካሪታስ ኢን ቨሪታተ - ፍቅር በሓቅ” በሚል ርዕስ ሥር የደረስዋት አዋዲት መልእክት ክርስትያናዊ ስነ ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ የሰው ልጅ የተሟላ እድገት በእውነት እና በፍቅር ላይ የጸና በዚህ ዓለማዊነት ትሥሥር እየተረጋገጠ ላለበተ ዓለም መሠረት ፍትህ ሰላም እኩልነት ይሆን ዘንድ የሚያነቃቃ እና የሚያስተምር መሆኑ ባለፈው RealAudioMP3 ማክሰኞ በቫቲካን የተገኙት የጀርመን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ኣቡነ ሮበርት ሶሊሽ መግለጣቸው ሲር የዜና አገግልሎት አስታውቀዋል።

ብፁዕ ኣቡነ ሶሊሽ “አዋዲጥ መልእክቷ የቤተክርስትያን የማኅበራዊ ትምርህት ምንኛ ወደ ፊት እያለ መሆኑ የምታበክር ነች” ካሉ በኋላ አያይዘውም “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ስለ ኤኮኖሚና ፖለቲካ በተመለከተ ትምህርት ለማስተላለፍ ሳይሆን እድገት የሚባለው ሂደት የዘነጋው የፍቅር በሓቅ መግለጫ የሆኑት ፍትሕ የጋራ ጥቅም እኵሉነት ያካተተ በጥቅላላ መሠረታውያን መመሪያዎች የሚባሉትን የማያስታውስ ያለማችን የኢኮኖሚውና የፖለቲካው ሂደት እይታው በነዚህ መሠረታውያን መመርያዎች ላይ ያጸና ይሆን የሚያሳስብ ነው ብለዋል።

የበልጅም ብፁዓን ጳጳሳትም ምክር ቤት ጭምር ተመሳሳይ አስተያየት የሰጡበት መሆናቸው ሲገለጥ ዓለማችን የሚከተለው የኤኮኖሚ እና የልማት ሂደት መሠረት ስነ ምግባርና ግብረ ገብ ይሆን ዘንድ ቅዱስነታቸው በደረስዋት አዋዲት መልእክት እንዳሳሰቡና ይኸንን ለማረጋገጥም መንገዱን እንዳመለከቱ እና ሥርዓት ዓልቦ የኤኮኖሚ ሂደት ያስከተለውን ችግር በመለየትም የመፍትሔው መሠረት ምን መሆኑ የምታሳስብ መሆኗ የበልጂም ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ አስታውቀዋል።

የፓሪስ ሊቀ ጳጳስ የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንድረ ቪንግ ትሮይስ “አለ የጋራ ጥቅም ዓላማና ግብረ ገብ፣ ኤኮኖሚ መሠረተ የሌለው እንደሚሆንና ይህ ደግሞ ምንም እንደሚያስከትል የተረጋገጥ ነው” በማለት “አዋዲት መልእክቷ ማንም ከግብረ ገብ ኃላፊነት ነጻ እንዳልሆነ የምታስተምር ነች” ብለዋል።

የአየር ላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በበኵሉም ር.ሊ.ጳ. በደረስዋት አዋዲት መልእክት በክርስትያናዊ አገላለጥ በሚሰጥና በሚቀበል ፍቅር ያለውን መጽሓፍ ቅዱሳዊ ቲዮሎጊያዊ አገላለጡን እና ኣኗኗኑርን በመከተል፣ ይህ ክብር ከእግዚአብሔርና ከጎረቤታችን ጋር ባለንን ግኑኝነት የምናሳየው ምግባረ ጥሩነት በኤኮኖሚውም ሂደት ይሁን በፖለቲካው ዓለም እንዴት መገለጥ እንዳለበት፣ ብሎም የሰው ዘር መሠረታዊ መብት ይከበር ዘንድ እና በሕይወት ለመኖር የሚያግዙት መሠረታዊ ፍላጎቶቹ እንዲጠበቁለት የምታሳስብና የምታስተምር አዋዲት መልእክት” መሆኗ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.