2009-07-11 08:17:41

ዓለም ዓቀፍ የሕፃናት አድን ድርጅት


ሰቭ ዘ ቺልድረን ዓለም አቀፍ የሕፃናት አድን ድርጅት በኢንዳስትሪ የበለጸጉት 8 አገሮች: በዚህ ባለማችን ተከስቶ ባለው የኤኮኖሚ መቃወስ ምክንያት፣ በተለያዩ ችግር የተጠቁት ድኾች ሕጻናት ለከፋ እደጋ እየተጋለጡ መሆናቸው RealAudioMP3 በመግለጥ፣ ህፃናትን በሚደረገው የትብብርና የድጋፍ እቅድ ቀዳሜውን ሥፍራ ይዘው እንዲገኙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በያመቱ ባለማችን 9.2 ሚሊዮን ሕጻናት በቀላሉ ለመከላከል በሚቻሉት በሽታዎች እና ችግሮች አማካኝነት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ድርጅቱ በመግለጥ፣ በኢንዳስትሪ የበለጸጉት አገሮች የእነዚህ ሕጻናት ችግር ለመቀረፍ ጥረት አያደርጉም በማለት ወቀሳውን በመሰንዘር፣ ለሕጻናት መርጃ እቅድ ማስፈጸሚያ የሚመደበው የገንዘብ ሃብት በእጥፍ ከፍ እንዲል ካልተደረገ ማለትም ቢያንስ ከ 7 ሚሊያርድ ካልተመደበ እ.ኤ.አ. እስከ 2012 ዓ.ም. የሕጻናት የሞት መጠን በግማሽ ዝቅ ለማድረግ የተወጠነው እቅድ በ 2045 ብቻ እንደሚደረስ ድርጅቱ በማሳሰብ፣ ሃብታም አገሮች ሕጻናት ለማዳን በሚደረገው ጥረት ቀዳሚውን ሥፍራ እንዲይዙና የሁሉም የመማር፣ የጤና እንክብካቤ አገልግሎትና ምግብ የማግኘት መብት እንዲረጋገጥም ድርጅቱ ባወጣው ሰነድ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.