2009-07-11 08:14:15

ክርስትያናዊ ስነ አብአዊነት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “ካሪታስ ኢን ቨሪታተ - ፍቅር በሐቅ በሚል ርዕስ ሥር የደረስዋት ዓዋዲት መልእክት በተለያዩ ያለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ዓቢይ ትኩረት ተሰጥቶባት ቀዳሚ ገጽ መሆኗ RealAudioMP3 እንዲሁም እዚህ ሮማ በመካሄድ ላይ ላለው የጂ 8 ማለትም የስምንቱ በኢንዳስትሩ የበለጸጉት አገሮች መሪዎች ጉባኤ መርህ ለመሆን እንደምትችል ቀደም ተብሎ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አስተያየት ተሰጥቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ በሚገኘው የኤኮኖሚ መንበረ ጥበብ የኤኮኖሚ ፖለቲካ መምህር ልዊጂኖ ብሩኒ፣ ይህች ዓዋዲት መልእክት በተመለከተ ለቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ሲመልሱ፣ “በአሁኑ ሰዓት ዓለማችን ስለ ኤኮኖሚና ገበያ በተመለከተ እየተደረገ ላለው ጥልቅ አስተንትኖ እና ጥናት መሠረት ነች” ብለዋል። “ገበያ ባንድ መልኩ ነጻና ግልጽ የሆነ አገናኝ አቀራራቢ ጉዳይ ሆኖ ሲገለጥ፣ በሌላው መልኩ ደግሞ በምግባረ ጥሩነት ያልተካነ በኢግብረ ገባዊነት የተበከለ ሆኖ ይገኛል፣ ይኸንን እግምት ውስጥ በማስገባትም የር.ሊ.ጳ. አዋዲት መልእክት በትክክል ለኤኮኖሚው ለፖሊቲካው ዓለም የተስተካከለ ሂደትና ተስፋ የምታሰጥና ፈር የምታስይዝ ነች” ብለዋል።

“በሌላው ረገድ መንፈሳዊው እና ቍሳዊው ዓለም በሚከፋፍል ባህል እየተመራ ይህ አመለካከትም በሁሉም መስክ የሁሉም መሠረት እየሆነ እያስከተለው ያለው ችግር በማጉላት የሕይወት አንድነት እምነትና ዕለታዊ ኑሮ ማዛመድ ግብረ ገብና ስነ ምግባር የተካነው ዓለማዊ ሂደት ማረጋገጥ ለኔ የሚለው ብቻ ሳይሆን ላንተ የሚለውን፣ የተቀበልከውን ለማካፈል ባጠቃላይ በፍቅር ላይ የተመሠረተ ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ሂደት ለማረጋገጥ የምትጠራና ይኽንን ለመፈጸም ምን መደረግ እንዳለበት የምታስተምር ነች” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.