2009-07-08 14:31:32

የር.ሊ.ጳ. አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ጥዋት በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ለተሰበሰቡት በብዙ ሺሕ ለሚገመቱት ምእመናን ሳምታዊው የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማቅረባቸው ተመለከተ። RealAudioMP3

ቅዱስነታቸ ሰፋ ያለውን አስተምህሮ የሰጡት በጣልያንኛ ቋንቋ ሲሆን፣ በመጨረሻ በተለያዩ ቋንቋዎች አጠር ያለ ተመሳሳይ ትምህርት አቅርበዋል።

ክቡራንና ክቡራት አድማጮቻችን ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ለእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በማሳጠር ያቀረቡት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚከተለው ነው፦

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ዛሬ ስለ አዲሲቷ ሓዋርያዊት መልእክቴ ስለ “ካሪታስ ኢን ቨሪታተ” ማስገንዘብና መግለጽ እፈልጋለሁ። ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድተኛ ፖፑሎሩም ፕሮግረሲዮ የሕዝቦች እድገት የተሰኘውን አዋዲ መልእክት ከጻፉት አርባ ዓመታት በኋላ ሌላ ማሕበራውያን ጉዳዮች የሚያጤን አዲስ መልእክት መጻፍ አስፈላገ፣ ፖፑሎሩም ፕሮግረሲዮ ስለ ሰው ዘር ደህንነት በእጅጉ አስፈላጊነት ያላቸውን ርእሶች የሚተነትን ሁለቱም ማለት ግለሰብና ኅብረተሰብ እውነተኛ ለውጥና መታደስ እንዲያደርግ የቤተክርስትያን ማህበራዊ ትምህርት እንደሚያስተምረው በፍቅር በክርስቶስ ሓቅ መኖር መቻል እንዳለባቸው ያሳስባል ሲሉ ሓዋርያ ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሰዎች ከጻፋት መልእክት ምዕራፍ አራት ቁጥር አስራ አምስት ላይ ያለውን “ይልቁንም እውነትን በፍቅር እየተናገርን ራስ የሆነውን ክርስቶስቶስን ለመምሰል በሁሉ ነገር እናድጋለን” የሚለውን ጠቀሱ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.