2009-07-08 13:15:27

ንጽሕና ድንግልና ክብረ ንጽህና


ከትላትና በስትያ በላቲን ሥርዓት የተከበረው የቅድስት ማሪያ ጎረቲ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ይህች ሰማዕት ቅድስት በተወለደችበት በኢጣሊያ በላቲና አውራጃ የምትገኘው የፈሪየረ ከተማ ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪያኖ ክሮቻታ ባሰሙት ስብከት RealAudioMP3 “ንጽሕና ድንግልና ክብረ ንጽህና ጉዳይ በተመለከተ ይቅር ለመናገርና ለማሰቡም የማይፈቅድ ኋላ ቀርነት የሚገልጥ ማለት እንደሆነ በሚያተምረው ባህል በተስፋፋበት ዓለም፣ ምንም ትርጉም የሌላቸው ሆነው ከማኅበረሰብ ማህበራዊ መዝገበ ቃላት ውጭ ሆነው፣ በዚህ የሐሰት ስድና ልቅ ነጻነት የሚሰበክበትና ሁሉም ይኸንን አመለካከት ገቢራዊ ለማድረግ መራወጥ በኃላፊነት ላይ ያልጸና ነጻነት-ባርነት መኖር ነው፣ የእኔ ሕይወት የግሌ ነው፣ ስለዚህ በግሌ የፈለኩት ባደረግ የእራሴ ጉዳይ ነው እየተባለ ትሕትና አወንታዊ አፍረት ተወግዶ እራስን በትክክል መውደድ ከዕለታዊው ኑሮ ውጭ እየሆነ ነው” ብለዋል።

“ሕይወታችን ትርጉም እንዳለው መገንዘብ እንደሚገባንና ትርጉም ካለው ደግሞ ሥርዓትን የተከተለ ኣካሄድ ሊኖር ይገባል እንጂ፣ መሆናችን እንዳሻኝ በሚል መሠረተ አልቦ በሆነው ለደመ ነፍሳዊ ሂደት ተገዥ መሆን የለበትም። በተለይ ደግሞ በተለያየ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ ሁሉ የስነ ምግባርና የግብረ ገብ ሕይወት አብነት መሆን ይገባቸዋል። ማህበራዊ እና ግላዊ ጉዳዮች የሚያገናኛቸው ምንም ነገር የለም እየተባለ በዚህ ዓይነቱ ልቅ አመለካከት የሚመሩ በተለያየ ኃላፊነት እና ጥሪ የሚኖሩ እንዳሉም” በማብራራት “ስለዚህ የመግናኛ ብዙኃንና በኃላፊነት ላይ የተቀመጡ በዕሴቶች ላይ የተመሠረተ ከምግባረ ጥሩነት ጋር የሚስማማ ሕይወት መስካሪያን መሆን፣ የሚሰጡት አብነት ሕይወትን የሚደግፍ እንጂ የሚያወድም መሆን የለበትም” እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.