2009-07-07 08:52:47

ፓሪስ፣ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፡ የስነ ጥበባትና የባህል ድርጅት ጉባኤ


RealAudioMP3 የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፡ የስነ ጥበባትና የባህል ድርጅት አዘጋጅነት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛው የትምህርት የአሰጣጥ ሥርዓት የተደቀነበት እክል ርእስ በማድረግ እንዲወያይ የጠራው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ትላትና በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ተከፍቷል።

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከሓምሌ 8 እስከ ሐምሌ 10 እዚህ በኢጣሊያ የሚካሄደው የስምንቱ በኢዱስትሪ የበለጸጉት አገሮች መሪዎች ጉባኤ ምክንያት በማድረግ፣ ጉባኤው ለሚያስተናግደው ለወቅቱ የማኅበሩ ተረኛ ሊቀመንበር ለኢጣሊያ መንግሥት መሪ ሲልቪዮ በርሉስኮኒ ባስተላለፉት መልእክት፣ “ለዴሞክራሲው ሥርዓት መረጋገጥ ህንፀት ወሳኝ ነው” ብለዋል። በዚህ በፓሪስ በሚካሄደው ጉባኤ የካቶሊክ ትምህርት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ህየንተ ብፁዕ ካርዲናል በሩገስ ዣን ልዊስ እና ዋና ጸሃፊ ክቡር አባ ፍረደሪክ ቤኪና እየተሳተፉ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፡ የስነ ጥበባትና የባህል ድርጅት የቅድስት መንበር ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ፎሎ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ “የላቀ የትምህርት ወይም የህንፀት ፍላጎት እና የከፍተኛ ትምህርት ጠያቂ ብዛት እያደገ መምጣቱ በመጥቀስ፣ ይኸንን ጉዳይ የሚከታተለው የፖሊቲካው ሥርዓት ይኸንን ፍላጎት ለማርካት እና የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት ትግባሬውን የሚመራ ፖሊቲካ ወሳኝ እና ከዚህ ፍላጎት ጋር የሚዛመድ ከጥያቄው ጋር ለመወያየት ብቃት ያለው መሆን ይገባል ብለዋል።

ይህ የፓሪስ ጉባኤ በእርግጥ የድሆች አገሮች ምሁራንና ሊቃውንት አገሮቻቸውን እየተዉ በገፍ እንድሚሰደዱና ይህ ዓይነቱ ችግርም ባንዳንድ የኤውሮጳ አገሮች ጭምር እያጋጠመ መሆኑ በመጥቀስ፣ ይህ ድኽነት እንዲባባስ ከሚያደርጉት ችግሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የምሁራን መሰደድ ክስተት ለመቅረፍ ብቃት ያለው፣ የትርምህት ፖለቲካ ደንብ እጅግ ወሳኝ መሆኑ ስለ ጉዳዩ ውይይት ይደረግበታል” ብለዋል።

“በዓለማችን 1300 የካቶሊክ መናብርተ ጥበባት እንዳሉም በመጥቀስ፣ እነዚህ የካቶሊክ የከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች የሚከተሉት የትምህርት ሥርዓት እና የትምህርት አሰጣት ደንብ በብዙ አገሮች መንግሥታት የሚደነቅ ነው። በዚህ አጋጣሚም ስለ ካቶሊክ ከፍተኛ ተቋሞች የትምህርት የአሰጣጡ ደንብ በይፋ ለጉባኤው ማብራሪያ ይሰጥበታል” ብለዋል።

በመጨረሻም “የትምህርት አሰጣጥ ደንብ ከአስተማሪዎች ጉዳይ ጋር የተጣመረ ነው። አስተማሪዎች አስፈላጊዎች ናቸው። ላንድ አገር ዕድገት ትምህርት ቤቶች እና አስተማሪዎች ወሳኞች ናቸው። ስለዚህ ማስተማሩ ዓቢይ ኃላፊነት መሆኑ እግምት ውስጥ በማስገባት አስተማሪዎች በቂ የደሞዝ ክፍያ ሊኖራቸውም ይገባል። ያስተማሪዎች የማስተማር ፍላጎት የሚያነቃቃ ተጨባጭ ዘዴ ማረጋገጥ ያስፈላጋል። አንዱን ተማሪ በተለያዩ የትምርት ዘርፎች ብቻ ማነፅ ሳይሆን ሰብአዊና ማኅበራዊ ህንፀት ጭምር ማግኘት ይኖርበታል” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.