2009-07-07 08:22:11

ስለ ደም ማፍሰስ

ሰዎች፣ ሕይወት ቅዱስ መሆኑን መቸ ያውቁ ይሆን?


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሁድ እኩለ ቀን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመምራታቸው በፊት እና በኋላ ባስተላለፉት መልእክት በዓለማችን በአመጽና በፍትሕ አልቦነት የሚፈሰው ደም ይቁም ሲሉ ተማጥነዋል።

የክርስቶስ ደም እግዚአብሔር ለሰው ዘር ያለው ታማኝ ፍቅር ዋስትና ነው። በምድራችን በተለያዩ ክፍሎች የሚፈሰው ደም ለሚያሰማው የጩኸት ድምፅ እግዚአብሔር መልስ የሚሰጠው በልጁ ደም ነው።

የመጨረሻ የስቃይ ጩኸት ድምፅ እየሰማን ያለነው ዛሬ ጥዋት በፊሊፒንስ አገር በኮታባቶ ካተድራል በራፍ በፈነዳውና የብዙ ሰው ሕይወት ባጠፋው የግብረ ሽበራ የጥፋት ድርጊት ሰበብ የተፈጠርውን ነው። ሲሉ ስለ አደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ሓዘን ገልጸው የሽበራ ድርጊት የችግር መፍትሔ አለመሆኑን በማረጋገጥ በአጽንኦት የአምጹን ተግባር ኮንነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.