2009-07-07 08:55:19

ሞስኮ-የተባበሩት ያሜሪካ መንግሥታት


RealAudioMP3 የተባበርቱ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ከሩሲያው አቻቸው መድቨደቭ ጋር ለመገናኘት ዛሬ ሞስኮ ገብተዋል። ግኑኝነቱ በተመለከተ የሩሲያው ርእሰ ብሔር መድቨደቭ ኮሬረ ደላ ሴራ ከተሰኘው የኢጣሊያው ዕለታዊ ጋዜጣ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ “የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት በምሥራቅ የኤውሮጳ አገሮች የህዋ የመከላከያ እቅድ ለመትከል ያላት ፍላጎት ሩሲያ በመሠረቱ በቅድመ ሁኔታ የምትቃወመው እንዳልሆነ በመጥቀስ፣ ስለ ጉዳዩ ከአዲሱ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ያመራር አካላት ጋር ባንድ ስምምነት ላይ ሊደረስ እንደሚቻል ነው” ካሉ በኋላ፣ “እራስን ለመከላከ በማቀድ የሚደረገው የህዋ የመከላከያ እቅድ ባንድዮሽ ውሳኔ ብቻ መረጋገጥ ያለበት ጉዳይ እንዳልሆነ፣ ሩሲያ አበክራ እንደምታምንበት” በመግለጥ “የጋራ ስምምነት አስፈላጊ ነው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.