2009-07-03 17:46:10

የአምነስት ኢንተርናሽናል ሰነድ


አምነስት ኢንተርናሺናል፤ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጓች ማኅበር፤ የእስራኤል የመከላከያ ኃይሎች በጋዛው ሰርጥ ክልል ለ 22 ቀን ጸረ ሓማስ ሰንዝረውት በነበረው ጥቃት ወቅት በነዚህ የእስራኤል ወታደሮች እና በሐማስ ታጣቂ ኃይሎች አማካኝነት በጋዛ ክልል የተፈጸመው የሰብአዊ መብትና ፈቃድ ረገጣ የሚያወሳ ልዩ የጥናት ሰነድ ይፋ ማድረጉ ተገለጠ።

አምነስት ኢንተርናሺናል ያቀረበው ሰነድ እስራኤል ሚዛን የሌለው ለአንዱ ወገን ያደላ የሐማስ ፍልጎት ሰለባና በዚህ የአሸባሪያን ኃይል በሚነዛው መግለጫ የተምታታ ነው በማለት የተቃውሞ ምላሽ ሰጥታበታለች።

ይህ የሰብአዊ መብት አስከባሪው የዓለም አቅፍ ማኅበር ያቀረበው ባለ 117 ገጽ ሰነድ እስራኤል እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ታኅሣሥ ወር በጋዛው ሰርጥ ለ 22 ቀናት ሰንዝራው በነበረውቸውን ጥቃት ከሐማስ ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት ያልነበራቸው የብዙ ፍልስጥኤማዊ ህዝብ ሕይወት መቀጨቱና የብዙ ሺ ህዝብ ቤት እና ንብረት መውደሙም በማተት እስራኤሉ በዚህ ሰንዝራው በነበረችው ጥቃት ሳቢያ የዓለም አቅፍ የጦርነት ጉዳይ የሚመለከተውን ሕግ መጣስዋ ተመልክቶበት ይገኛል። በጦርነቱ ሳቢያ 300 ሕጻናት የሚገኙባቸው 1400 ፍልስጥኤማውያን ለሞት መዳረጋቸው አምነስት ኢንተርናሺናል በመግለጥ የተባበሩት መንግሥታት በጋዛው ሠርጥ ተካሂዶ ስለ ነበረው ጦርነት ጉዳይ የሚመረምር ድርገት በሚያካሂደው የማጣራት ሥራ የእስራኤል መንግሥት እና የአገሪቱ የመከላከያ ኃይል የበላይ አዛዦች ለመተባበር ፈቃደኞች ሆነው ባለ መገኘታቸው ምክንያት በመንቀፍ ስለዚህ ትብብር እንዲኖር ጥሪ ያቀርባል።

ለአምነስት ኢንተርናሺናል በጋዛው ሠርጥ ተጠሪ ዶናተላ ሮቨራ በጋዛው ሰርጥ ስለ ተካሄደው ጦርነት ሓቁን ለማወቅ አጣሪው ድርገት ወሳኝ ሚና ያለው ብቸኛ መሣሪያ ነው ሲሉ፣ ያምነስስት ኢንተርናሺል ሰነድ ሐማስ ወደ ያይሁዳውያን መኖሪያ የእስራኤል ክልሎች በፍንዳታ ሮኬት የተሸኘ ጥቃትንም ጭምር የሚያወግዝ ሰነድ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.