2009-06-17 17:21:17

የትምህርት ገበታ ለሁሉም


ቋሚ መኖሪያ የሌላቸው የዘላኖች ቤተሰብ ልጆች ተገቢ የትምህርት እድል ያገኙ ዘንድ ቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ ማኅበር የተለያዩ እቅዶችን በመወጠን ዓቢይ የሕንጸት መርሃ ግብር እያከናወነ ነው። በኢጣሊያ ለ17 ሺሕ 400 የዘላን ቤተሰብ ልጆች የትምህርት ዕድል መረጋገጡ ማኅበሩ ካወጣው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል። RealAudioMP3

በዚህ ማኅበር የተጀመረው ለዘላኖች ቤተሰብ ልጆት የትምህርት ዕድል ማረጋገጥ መርሃ ግብር አጥጋቢ ውጤት እያስገኘ መሆኑ የማኅበር ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓሊያዞ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አብራርተዋል።

ይህ ማኅበር በመላ ኢጣሊያ ከተሞች እያካሄደው ያለው ለዘላኖች ቤተሰብ ልጆች ትምህርት የማግኘት መብት ዋስትና የመስጠቱ ዕቅድ ገቢራዊ ለማድረግ የሚጠይቀው የገንዘብ ወጪ ከተለያዩ መልካም ፈቃድ ካላቸው ዜጎችና እቅዱ ለሰላማዊው ማኅበራዊ ሕይወት ወሳኝ መሆኑ ከሚያምኑበት መንግሥታት ጭምር እንደተገኘም ኢምፓሊያዞ ገልጠው፣ እቅዱ በኢጣሊያ ብቻ ሳይታጠር በእስያ ላቲን ኣሜሪካ እና ባፍሪካ ጭምር እየተስፋፋ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.