2009-06-15 15:11:26

ዓመተ ክህነት


እፊታችን ዓርብ እ.ኤ.አ. ሰነ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት የቅዱስ ልበ ኢየሱስ በዓል በሚከበርበት ዕለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በሚመሩት ጸሎተ ሠርክ የክህነት ዓመት በይፋ ይከፍታሉ። RealAudioMP3

ይህ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሚያወጁት ዓመተ ክህነት፣ ካህናት የተጠሩበት ዓላማ ፍሪያማነቱና አጥጋቢነቱ ወደ ሚያጸናው መንፈሳዊው ፍጽምና ያቀኑ ዘንድ በማሰብ ባለፈው ዓመት የክህነት ዓመት ባወጁበት ዕለት መግለጣቸው የሚዘከር ነው። ስለዚሁ እፊታችን ዓርብ የሚጀመረው ዓመተ ክህነት በማስመልከት የቅድስት መንበር የዜናና የማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረድዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ሎምባርዲ፣ “ካህናት ጸላያን መሆን ይገባቸዋል፣ መጸለይ እንደሚገባቸው ማስታወስ ይኖርባቸዋል በማለት ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አበክረው ካህናትን በሚቀበሉበት ወቅት ቅዱስ መቍጠርያም በሚሰጡበት ወቅት የሚያቀርቡትን ጥሪ ለዚህ ዓመተ ክህነት መሠረት ነው” ብለዋል። “ዓመቱም የካህናት ጠባቂና አብነት የሆነው ቅዱስ ዮሓንስ ዘ ማርያም ቪያነይ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት 150ኛው ዓመት የሚዘከርበት ዓመት በመሆኑም ያስተላለፉትን አደራ ዓቢይና ጥልቅ ትርጉም የሚያሰጠው ነው” ብለዋል። “ብዙውን ጊዜ ካህን በሌላ ሌላ ሥራ ወይንም በሰብአዊው ረገድ ብቻ በመራወጥ የጥሪው መሠረት የሆነውን እየዘነጋ በችኮላና በልማድ ጸሎት ሲደግም ይታያል፣ እያንዳንዱ ክርስትያን ከእግዚአብሔር ጋር ምን ያክል ግኑኝነት አለው ተብሎ እራሱን እንዲመረምር ጥሪ የሚቀርብለት ከሆነ፣ ለካህን ጥያቄው ከፍ ብሎ እንደሚቀርብ ለመገመቱ አያዳግትም። ሁሉም ለቅድስና ነው የተጠራው፣ ሆኖም ግን ካህን በጥሪው አማካኝነት የሚኖረው ሕይወት ቅድስና የተሞላው ተቀድሶ የሚቀድስ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል። ስለዚህ ሓላፊነቱ ቀላል አይደለም። ሁላችን እንደምናውቀው አንዳንድ ካህናት ከጥሪያቸው ሲሰናከሉና እንቅፋት ሆነው ሲገኙ ምንኛ የቤተ ክርስትያንን ታማኝነቷን እንደሚነካ ለሁሉም ግልጽ ነው። ሆኖም ግን ቤተ ክርስትያን ቅድስት መሆኗ መዘንጋት የለበትም ብለው፣ የካህን ኃላፊነት ከባድ ቢሆንም ቅሉ በጸሎት የተደገፈ ከሆነ የጠራው እግዚአብሔር ኃይል ሆኖ ይደግፋል” ብለዋል።

ይህ የካህን ዓመት በመላ ዓለም በሚገኙት የካቶሊክ አባያተ ክርስትያንና ሰበካዎች እፊታችን ዓርብ ሰኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በይፋ እንደሚከፈት ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.