2009-06-10 15:35:06

የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ


የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ዓለማችንን እያናጋ ያለው የኤኮኖሚና የፋይናንስ መቃወስና እያስከተለው ያለው ማኅበረ-ምጣኔ ሃብታዊ ችግር መሠረት በማድረግ ትላንትና በክሮአዚያ ዛጋብሪያ ከተማ መሰብሰባቸው ተገለጠ። RealAudioMP3

ይህ የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የማኅበራዊ ጉዳይ በሚመለከተው ድርገት አማካኝነት ያካሄደው ስብሰባ ከ 21 የኤወሮጳ አገሮች የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ የተውጣጡ 34 ብፁዓን ጳጳሳት ያሰባሰበው ጉባኤ፣ የዛጋብሪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆሲፕ ቦዛኒች የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት ተከፍቶ በንግግር ያስጀመሩት ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ኣቡነ ጃምፓውሎ ክረፓልዲ ናቸው።

ብፁዕ አቡነ ክረፓልዲ “እ.ኤ.አ. 2008 ዓ.ም. በገንዘብ ሃብትና በተጨባጩ ኤኮኖሚ መቃወስ የተጠቃ ዓመት እንደነበርና እሁኑም ገና መፍትሄ ያላገኘ መሆኑም” አብራርተው “በድኻው ያለማችን ማኅብረሰብ ክፍል ላይ እስከተለው ያለው ችግር ዓቢይ ነው፣ ስለዚህ ቤተ ክርስትያን ጉዳዩ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የሁሉም በተለይ ደግሞ የአለም መግሥታት ኅሊና በማነቃቃት ላይ እንደምትገኝ” ገልጠዋል።

“የኤኮኖሚው ቀውስ ዓበይት የኤኮኖሚ አውታሮችና እያንዳንዱ ዜጋ በየዕለቱ የተጨባጭ የሚኖረው ጉዳይ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ክሬፓልዲ በማብራራት የተከስተው ቀውስ ኤኮኖሚና የፋይናንስ ሥርዓት አለ እሰይታና ሥነ ምግባር የት እንደሚያደርስ የሚገልጥ ተጨባጭ ምስክረትነት ነው ብለዋል። ስለ ኤኮኖሚ ለማሰብና ዕድገት ለማረጋገጥ ከተፈለገ ድኻውን የማኅበረሰብ ክፍል እግምት ውስጥ ማስገባት ተቀዳሚ ውሳኔ መሆን ይገባዋል፣ ካልሆነ ለውጥ ወይንም መሻሻል ይረጋገጣል ብሎ ማሰብ እራስ ማታለል ነው” ብለዋል።

ለተጋባእያን የእንኳንድ ደህና መጣችሁ ንግግር ያሰሙት ብፁዕ ካርዲናል ቦዛኒች “ቤተ ክርስትያን ዘወትር የሰው ልጅ ማዕከል በማድረግ የሰው ልጅ መብትና ፈቃድ ሰብአዊ ክብሩ የጋራ ጥቅም እንዲረጋገጥ የመሥራት መብትና ድኻው ማህበረሰብ ልዩ ድጋፍ እደሚያሻው ግዴታ መሆኑ ዘወትር በቃልና በሕይወት ታስተምራልቸው ኅሊናን ታነቃቃለች” እንዳሉም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.