2009-06-10 15:48:39

የ2009 ዓ.ም. የግብረ ሠናይ ሽልማት


2009 ዓ.ም. የግብረ ሠናይ ሽልማት ለባንግሊዴሽ ዜጋ ለሆኑት ለፕሮፈሶር ኢብራሒም ሙሓማድ ባለፈው ዓርብ በስዊዘር ላንድ የሉቸርና የባህል ተቋም አዳራሽ መሰጠቱ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ፕሮፈሶር ሙሓማድ ለዚህ ሽልማት የበቁበት ምክንያት፣ “በዚህች እጅግ ድኾች አገሮች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ ቀዳሚውን ደረጃ ይዛ በምትገኝ የባንግላደሽ አገር ድኽነት እንዲቀረፍ የሚሰጡት ህንጸት መሆኑ ተገልጠዋል። እኚህ 64 ዓመት እድሜ ያላቸው በባንግላደሽ ርዕሰ ከተማ ዳካ በሚገኘው መንበረ ጥበብ የፊሲኪስ መምህር የማህበራዊ ህንጸት ማዕከል አባል በመሆን ድኽነት እንዲቀረፍ በሚሰጠው የህንጸት መርሃ ግብር መሳተፍ ከጀመሩ 30ኛውን ዓመታቸውን ያገባደዱ በግል ወይንም በማኅበር ደረጃ የኤኮኖሚ ድርጅት በማቋቋም እራስን መቻል የሚያግዝ መሠረታዊው ትምህርት በመስጠት የተጉ ሰብአዊና ማህበራዊ ህጽነት በመስጠት ሰብአዊነትን ማዕከል ያደረገ የኤኮኖሚ ድኽነትን ለመቅረፍ መሠረት መሆኑ የሚያስተምሩ፣ የተፈጥሮ ሃብትና ያካባቢ ጤንነት የማይጎዳ የኤኮኖሚ ስልት የሚያነቃቁ የአለም አቀፍ የምግብ ድርጅትና የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፡ የስነ ጥበባትና የባህል ድርጅት አባል መሆናቸውም ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.