2009-06-10 15:40:37

ከማቸራታ ወደ ሎረቶ የሚደረገው የእግር ንግደት ወይም መንፈሳዊ የእግር ጉዞ


በኢጣሊያ ‘ኮሙኒዮነ ኤ ሊበራዚዮነ’ ውህደትና ነጻነት የተሰኘው ማኅበር አነሳሽነት በየዓመቱ ከማቸራታ እስከ ሎሬቶ የሚካሄደው ንግደት/መንፈሳዊ የእግር ጉዞ፣ RealAudioMP3 ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፋት አንደኛይቱ መልእክት ምዕራፍ 4 ቍጥር 10 “በሕያው እግዚአብሔር ተስፋ ስለ ምናደርግ ነው” በሚል መንፈሳው መርኆ የተሸኘ እንደሚሆን የዘንድሮው 31ኛው መንፈሳዊ የእግር ጉዞ መርኃ ግብር በይፋ በቀረበበት ዕለት ተገልጠዋል።

ይህ የዛሬ 30 ዓመት በፊት በዚህ የኮሙኒዮነ ኤ ሊበራዚዮነ ማኅበር ወጣት አባላት ዓመታዊ የትምህርት ዘመን ማገባደጃ ምክንያት እግዚአብሔር ለሰጣቸው ጸጋ ሁሉ ለማመስገን አቅደው የጀመሩት መንፈሳዊ የእግር ጉዞ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ ስኔ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚካሄደው መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ምክንያት የሚቀርበው መስዋዕተ ቅዳሴ የናፖሊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ክረሼንዚዮ ሰፐ በ ላኵይላ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ጁዜፐ ሞሊናሪ ታጅበው እንደሚመሩት ተገልጠዋል።

ይህ መንፈሳዊ የእግር ጉዞ የእምነት የተስፋና የፍቅር አብነት የሆነቸው የቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳዊነት መሠረት በማድረግ የሚከናወን መሆኑም ሲገለጥ፣ ማርያም የነጻነት እና የአንድነት አብነት መሆኗ የሚመሰከርበትና ባለማችን የሕይወት ክብርና የሃይማኖት ነጻነት እንዲረጋገጥ የሚጸለይበት የሚጠየቅበት እለት መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.