2009-05-29 15:22:32

የኢራቅ ማኅበረ ክርስትያን


በኢራቅ በተለይ ደግሞ በባግዳድ የሚኖሩት የአገሪቱ ማኅበረ-ክርስትያን ላይ ምክንያቱ ገና እውን ያልሆነ ለድጋፍና እርዳታ ለማቅረብ እየተባለ በአንዳንድ ግለ ሰዎች የክርስትያን ሕዝብ የብዛት የንብረት ቆጠራ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑ በመጥቀስ የአገሪቱ ከለዳውያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢና ሕልውናን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ገሃድ አድረገዋል።
RealAudioMP3 ይህ ጉዳይ ምን ያስከትል ይሆን ለሚለው ጥያቄ የፓክስ ክርስቲ ማለትም የሰላመ-ክርስቶስ ማኅበር ተጠሪ ኣባ ሬናቶ ሳኮ ከቫቲካን ረድዮ ለቀረበላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፣ “ክርስትያኖችን ለይቶ መመዝገቡ ምናልባት ለመቆጣጠር ሊያመች ተብሎ ሊሆን ይችላል፣ ይህ ማለት ግን ሌላ አደገኛ ምሥጢር ያለውም ሊሆን ይችላል። ለምንስ ክርስትያኖች ብቻ ለይቶ ብዛታቸው ለማወቅ ተፈለገ? በኢራቅ ውሁዳን የህብረተሰቡ ክፍል ላይ የተከሰተውና ገና በመከሰት ላይ ያሉ ችግሮች እግምት ውስጥ በማስገባት እየተከናወነ ያለው የብዛትና የባለ ንብረትነት ቆጠራ አሳሳቢ ነው” ብለዋል።

“የኢራቅ ክርስትያኖች ለራስ ደህንነት ሲባል አገራቸው እየለቀቁ ወደ ተለያዩ አገሮች በመሰደድ ላይ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ በዚህ ክልል መረጋጋት እንደሌለ የሚያረጋግጥ ምርጫ ነው። ስለዚህ እየተከናወነ ያለው የክርስትያኖች ብዛትና የንብረት ቆጠራው ጉዳይ ምን ዓላማ እንዳለው በክልሉ ካለው አለ መረጋገት አንጻር ሲታይ የሚያሳስብ ነው። ር.ሊ.ጳ. በቅርቡ በመካከለኛው ምሥራቅ ሓዋርያዊ ጉብኝት ሲያካሄዱ የሚለያዩ ግንቦች ሳይሆን የሚያገናኙ ድልድዮችን እንገባ እንዳሉ አባ ሳኮ አስታውሰው በኢራቅ የተለያዩ ጎሳዎችና ሃይማኖቶችን የሚያቀራርብ ድልድይ ለክልሉ መረጋጋት መሠረት ነው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.