2009-05-20 15:28:37

የህንድ ሕዝባዊ ምርጫ


RealAudioMP3 በህንድ በቅርቡ በተካሂደው ሕዝባዊ ምርጫ በሶኒያ ጋንድሂ በሚመራው የህንድ ሕዝባዊ ጉባኤ የፖለቲካው ሠልፍ የሚመራው ቅይጡ የፖለቲካ ሰልፍ በስፋት ማሸነፉ ይታወሳል። ብሔርተኛው ሂንዱ የፖለቲካ ሰልፍ በተካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ እንደሚያሸንፍ በይፋ የታመነበት እንደነበርና የተገኘው የምርጫው ውጤት ላገሪቱ ውሁዳን ማኅበረሰብ እና ለሃይማኖት ነጻነት ዋስትና ነው ተብለዋል።

የተገኘው ውጤት በማስመልከት በህንድ የራንቺ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ተለስፎሮ ፕላስዱስ ቶፖ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “የህንድ ሕዝብ ስለ ዴሞክራሲ ሥርዓት አጥጋቢ ግንዛቤ ያለው መሆኑ የሚታወቅ ነው፣ ካለ ማንም ግፊትና ተጽእኖ አራሱ አስቦና ወስኖ ድምጽ የመስጠት ብቃት ያለው ነው” ብለዋል።

“ሕዝባዊ ጉባኤ የፖለቲካው ሠልፍ ያሸንፋል የሚል ግምት ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ቅሉ እንዲህ ባለ ሰፊ ድምጽ ያሸንፋል ብሎ ያሰበ ያለ አይመስለኝም፣ የህንድ ሕዝብ ይመራኛል ያለውን የፖሊቲካ ሰልፍ መርጠዋል፣ በማለት ቀጥለውም “ባለፈው በጋ በኦሪሳ ተቀጣጥሎ የነበረው ጸረ ክርስትያን አመጽ የህንድ መራኄ መንግሥት ማሆሃን ሲንግ የዓመጹ ድርጊት ብሔራዊ ሓፍረት ነው” ብለው በመግለጥ “መንግሥታቸው የዚህ ዓይነት ተመሳሳይ የማኅበራዊ ሰላም መሰናክል ዳግም እንዳይከሰት አበክሮ ይሠራል” እንዳሉም ዘክረው “ሆኖም ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተወግደዋል ለማለት እንደማይቻል ነው” ብለዋል።

“ቤተ ክርስትያን በአገሪቱ የውሁዳን ሃይማኖቶችና ማኅበረሰብ መብትና ፈቃድ ይከበር ዘንድ ዘወትር እንደምትጠይቅም” ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.