Home Archivio
2009-05-11 13:43:18
ፓኪስታን
የፓኪስታን የመከላከያ ኃይል ባገሪቱ ሽዋት ሸለቆ ክልል የሚገኙትን የጣሊባን ታጣቂ ኃይሎችን ለማጥፋት በሰነዘሩት ጥቃት ሳቢያ ከ 180 እስከ 200 የጣሊባን ታጣቂ አባላት ለሞት መዳረጋቸው የፓኪስታን የመከላከያ ኃይል መግለጫ ይጠቁማል። የዚሁ ክልል ነዋሪው ሕዝብ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ ለመፈናቀል መገደዱ ሲገለጥ፣ ክልሉን ለቆ ለመውጣት እንዲችልም የፓኪስታን መንግሥት በዚሁ ክልል የደነገገው የሰዓት እላፊ አዋጅ ማንሳቱ ተገልጠዋል።
የተባበሩት መንግሥታት መግለጫ እንደሚያመለክተውም፣ የፓኪስታን የመከላከያ ኃይል እየሰነዘረው ባለው መጠነ ሰፊ ጥቃት ሳቢያ 200 ሺሕ የክልሉ ነዋሪ ሕዝብ ለመፈናቀል አደጋ መጋለጡ ሲታወቅ ሌሎች 300 ሺሕ ጭምር በአሁኑ ሰዓት ክልሉን ለቀው እየወጡ መሆናቸ ሲገለጥ፣ በጠቅላላ 550 ሺሕ ህዝብ መፈናቀሉ የተባበሩት መንግሥታት መግለጫ ይጠቁማል።
All the contents on this site are copyrighted ©.