2009-05-06 12:09:16

የላቲን አሜሪካና የካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጉባኤ


የላቲን አሜሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት 32ኛው ይፋዊ ጉባኤው እ.ኤ.አ. ከግንቦት 11 ቀን እስከ ግንቦት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በኒካራጉዋይ ርእሰ ከተማ ማናጉዋ እንደሚያካሂድ ሲገለጥ፣ ይህ ከተለያዩ 22 የላቲን አሜሪካ ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የተወጣጡ 60 ብፁዓን ጳጳሳትን የሚያሰባስበው ጉባኤ፣ በዚሁ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ የሚገመግምና በዚሁ ጉዳይ ላይ በማስተንተንም የሚመክር መሆኑ ተገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችንን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛን ወክለው ጉባኤው የሚሳተፉትም የብጹዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተና የላቲን አሜሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጆቫኒ ባቲስታ ረ ሲሆኑ፣ በጉባኤው የካቶሊክ ቤተክርስትያንን የሚደገፉ የግብረ ሰናይ ማህበራት ተወካዮች ጭምር ይሳተፋሉ። የኒካራጉዋይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሶክራተስ ሬኔ ሳንዲኖ እንደገለጡት ይህ በኒካራጉዋይ የሚካሄደው ጉባኤ፣ እ.ኤ.አ. 2007 ዓ.ም. በብራዚል አፓሬሲዳ ከተማ የተካሄደው የላቲን አሜሪካና የካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጉባኤ የወጠነው የሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ መርህ፣ ሂደቱና ፍጻሜውንም እንደሚገመግም ለማወቅ ሲቻል፣ ጉባኤው የዚሁ የላቲን አሜሪካና የካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ በመህን እያገለገሉ ያሉትን በሜክሲኮ የፑዌብላ ሊቀ ጳጳሳት እንዲሆኑ እ.ኤ.አ. ባለፈው ሚያዝያ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ቪክቶር ሳንቸዝ ኤስፒኖሳን የሚተኩ ጭምር እንደሚመርጥም ሲታወቅ፣ በሌላው ረገድ ባለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ በዚሁ ክልል እያስከተለው ያለው ችግርና ከሜክሲኮ ተነሳ የሚባለው አዲሱ ተዛማች የአሳማ ጉንፋን ርእሰ በማስደገፍም ውይይት እንደሚያደርግም ብፁዕ አቡነ ሬኖ ሳንዲኖ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.