2009-04-27 16:19:02

የተባበሩት የሰሜን አመሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዒራቅ፡


የተባበሩት የሰሜን አመሪካ መንግሥታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ዒራቅ ላይ ያልታሰበ እና ያልተነገረ ጉብኝት ማድረጋቸው ከባቅዳድ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።
የዒራቅ ሁኔታ ፍጹም አስተማማኝ አለመሆኑ እና በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች የተካሄዱ ጥቃቶች 160 ሰዎች ሕይወታቸው እንዳጡ ተመልክተዋል።
የተባበሩት የሰሜን አመሪካ መንግሥት ዒራቅ ውስጥ ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት ቀጣይ ጥረት እንደምታካሄድ ሂላሪ ክሊንተን ባቅዳድ እንደገቡ መግለጻቸው ተነግረዋል።
ሂላሪ ክሊንተን ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑሪ አልማሊቂ እና እዚያው ከሚገኙ የአመሪካ ሰራዊት ጋር መገናኘታቸው ተገልጠዋል።
የዒራቅ አክራሪዎች የሚፈጽሙት የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት የዒራቅ ሰላም እና ልማት ለማስተጓጐል መሆኑ ሂላሪ ክሊንትን እንደገለጡ ተመልክተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.