2018-07-07 17:48:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ያለክርስቲያኖች የመካከለኛው ምስራቅ የመካከለኛው ምስራቅ ብለን ልንጠራአንችልም።


ር.ሊ.ጳ.ፍራንቸስኮስ፡ ያለክርስቲያኖች የመካከለኛው ምስራቅ የመካከለኛው ምስራቅ ብለን ልንጠራአንችልም።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው ዕለት ማለትም በሰኔ 30/3010 ዓ.ም የጣሊያን ግዛት ወደ ሆነችው ባሪ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ እዚያው ማቅናታቸው ይታወሳል። ይህ የቅዱስነታቸው ሐዋሪያዊ ጉብኚት አንድ ለየት ያለ ሐዋሪያዊ ጉብኝት መሆኑን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህንን የቅዱስነታቸውን ሐዋሪያዊ ጉብኚት ለየት የሚያደርገው ምክንያት የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ተወካዮች  በተለይም ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ የሐይማኖት መሪዎች መገኘታቸው ሰለሐይማኖት ሕብረት እና በተለይም ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ ክርስቲያኖች እና በመላው ማሕበረሰብ ላይ እየደረሰ ለሚገኘው ስቃይ እና ለቅሶ በጋራ በመሆን ጸሎት ማድረሳቸው ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደርጉት የመግቢያ ጸሎት እንደ ገለጹት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ማስፈን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደርጉትን የመግቢያ ጸሎት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 

የተከበራችሁ ወንድሞቼ

በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ ሕዝቦች ላይ እና እንዲሁም በአጠቃላይ በመላው ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ታላቅ የሆነ ስቃይ በልባችን ይዘን ወደ እዚህ ወደ ባሪ መንፈሳዊ ንግደት ለማድረግ መጥተናል። ለእነዚህ በስቃይ ላይ ለሚገኙ ሕዝቦችእኛም ከእናንተ ጋር ነንለማለት እንወዳለን። የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ!  እዚህ ከልብ በመነጨ መልኩ እና በፈቃደኝነት ወደ እዚህ በመምጣታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ። በእዚህ ከተማ ውስጥ ይህንን ሐዋሪያዊ ጉብኝት በማዘጋጀት እንድንገናኝ እንድንቀባበል ያደርጉትን ሰዎች ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

በአንድነት የምናደርገውን ጉዞ የእግዚኣብሔር እናት ትደግፈዋለች። ይህቺ እናት እዚህ በባሪ ከተማ በጣሊነኛ Hodegetria” ማለትም መንገድ የምታሳየን እናት በመባል ትከበራለች። በእዚህች ከተማ የምስራቃዊያን ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የነበረው እና ድንበር የለሽ በሆነ መልኩ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ድንበር መሸጋገሪያ ድልድይ በመሆን ያገናኘው የቅዱስ ኒኮላስ ቅዱስ አጽም የሚገኝበት ከተማ ነው። አስደናቂ ተዐምር ሠሪ የነበረው ቅዱስ ኒኮላስ ብዙ ሰዎች በውስጣቸው የሚገኘውን ቁስል  ይፈወስ ዘንድ ያማልደን። እዚህ በአድማስ እና በባሕር አጠገብ ሆነን ስናሰላስል በመካከለኛው ምስራቅ የሥልጣኔ መሻገሪያ እና ታላላቅ በአንድ አምላክ የሚያምኑ ሐይማኖቶች መገኛ እና ጥንታዊ እምነቶች መሠረት የሆነውን የመካከለኛው ምስራቅ በልባችን እና በአእምሮዋችን በማሰብ ነው።

የንጋት ፀሓይ (ሉቃስ 178) የሆነው ጌታ ወደ እኛ የመጣው ከመካከለኛው ምስራቅ ነው። ከእዚያም የእምነት ብርሃን በመላው ዓለም ተሰራጨ። መቼም ቢሆን ትኩስ የሆነ መንፈሳዊነት እና በአንድ አምላክ የሚያምኑ ሐይማኖቶች የመነጩት ከእዚያው ስፍራ ነው። በጣም ጥንታዊ እና ልዩ የሆኑ የስረዓተ አምልኮ ስነ-ስረዓቶች፣ ቅዱስ ከሆኑ ስነ-ጥበቦች እና የነገረ-መለኮት አስተምህሮች ጋር በጋራ ተጠብቀው የሚገኙበት ሥፍራ ነው። በእዚያም ውስጥ የእኛ ታላላቅ አባቶቻችን ውርስ ይገኛል። ይህንን ባህል በተቻለን መጠን ጠብቀን ልናቆየው የሚገባን ውድ የሆነ ሀብት ነው፣ ምክንያቱም የነብሳችን ሥር መሰረት የሚገኘው በመካከለኛው ምስራቅ በመሆኑ የተነሳ ነው።

ነገር ግን በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጣም ደማቅ የሆነ ይህ አካባቢ በጨለማ ደመናዎች፣ በሃይል እና በጥፋቶች፣ በጠለፋዎች እና በዘር ልዩነት፣ በአስገዳጅ ስደት እና ቸልተኛነት ተሸፍኖአል። ይህ ሁሉ ስቃይ እየተከሰተ የሚገኘው በብዙ ሰዎች ዝምታ የተነሳ ነው። የመካከለኛው ምስራቅ የራሳቸውን አገራት ወደ ኃላ ጥለው የመጡ ሰዎች ሀገር ሆኗዋል። በእምነት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሆኑ ሰዎች የሚገኙበት ሥፍራ በመሆኑ የተነሳ በእነርሱም ላይ ይህ ጉዳይ አደጋ ደቅኑዋል፣ ይህም የአከባቢውን ገጽታ ያበላሸዋል። ያለ ክርስቲያኖች የመካከለኛው ምሥራቅን የመካከለኛ ምስራቅ ብለን ልንጠራው አንችልም።

ይህንን ቀን ዛሬ እኛ የጀመርነው በጸሎት ሲሆን የእግዚአብሔር ብርሃን የዓለምን ጨለማ እንዲገፍ እንመኛለን። ቀደም ሲል በእዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ በሚገኘው የቅዱስ ኒኮላስ ቅዱስ አጽም ፊት ለፊት የአንድ ቤተ ክርስቲያን ተምሳሌት የሆነውን "አንድ ሻማበጋራ አቀጣጥለናል። ዛሬ በአንድነት የተስፋ ብርሃን መለኮስ እንፈልጋለን። የምናበራው መብራት በጨለማ ውስጥ ማብራት የሚችሉ መብራቶች ሆነው እንዲቀጥሉ እናመኛለን። ክርስቲያኖች የዓለም ብርሃን ናቸው (ማቴ 5 14) ሁሉም ነገር በዙሪያቸው ብሩህ በሚሆንበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ በታሪክ ውስጥ ጨለማዎች በሚፈጠሩበት ወቅት የጨለማውን ቦታ ለማስለቀቅ እና በተቃራኒው የተስፋ ብርሃን በመመገብ፣ ይልቁንም የተስፋውን ሽታ በመጠባበቅ እና በፍቅር እና በጸሎት ልተጉ ገባል። እጆቻችንን ወደ ሰማይ በጸሎት በማንሳት እና የራሳችንን ጥቅም ሳናስቀድም ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን እጆቻችንን ስንዘረጋ፣ ከዚያም የመንፈስ ቅዱስ እሳት፣ የአንድነት እና የሰላም መንፈስ እሳት ይነዳል ወደ ነበልባልነት ይቀየራል።

በአንድነት ሆነን በመጸለይ የዓለም ኃያላን ሀገራት ማምጣት ያልቻሉትን ሰላም ሰማይ አባታችን እንዲሰጠን ልንለምነው የገባል። ከአባይ ወንዝ ጀምሮ እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ከእዚያም ባሻገር በሚገኙ ሰርጦች ውስጥ፣ ጤግሮስ ወንዝ አንስቶ እስከ ኤፍራጠስ ወንዝ ደረስበውስጥሽ ሰላም ይስፈን” (መዝ. 1228) የሚለው የዳዊት መዝሙር ያስተጋባ ዘንድ ልንጸልይ ይገባል። በስቃይ ወስጥ ለሚገኙ እህት እና ወንድሞቻችን፣ ወዳጆቻችን ለሆኑ ሕዝቦች ሁሉ እና ተመሳሳየ የሆነ ጸሎተ ሐይማኖት ለሚደግሙ ሰዎች ሁሉ በተደጋጋሚሰላም በእናንተ ላይ ይሁንለማለት እንፈልጋለን። ቅድስት እና በእግዚኣብሔር ለተወደደች ነገር ግን በብዙዎቹ ለቆሰለቺው ከተማ፣ ጌታ በቀጣይነት ለሚያለቅስላት ከተማ ኢየሩሳሌም  ከዘማሪው ዳዊት ጋር በመሆንሰላም በአንቺ ላይ ይሁን” የሚለውን ጸሎት በተደጋጋሚ ልንጸልይ  ይገባል።

ሰላም ይሁን! ይህ ዛሬ እንደ አቤል የሚጮኹ ሰዎች የሚያቀርቡት ወደ እግዚአብሔር ዙፋን የሚወጣ ጩኸት ነው። ለእነሱ ስንል እኛም በመካከለኛው ምስራቅ እና በዓለም ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች "እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ ወይ?” (ዘፍጥረት 49) በማለት በግድዬለሽነት መንፈስ ልንቀመጥ አንችልም። ግድዬለሽነት ይገላል፣ ስለእዚህ እኛ ይህንን ገዳይ የሆነ የግድዬለሽነት መንፈስ በማስወገድ የተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድገን ማሰማት ይኖርብናል። እንዲያው ዝም ብለው እንባቸውን ለሚያፈሱ ድምጽ አልባ ለሆኑ ሰዎች እኛ ለእነዚህ ዓይነት ሰዎች ድምጽ ለመሆን እንፈልጋለን። ዛሬ በመካከለኛው ምስራቅ ኃይላቸውን ለማጠናከር ወይንም በእዚያ የሚገኘውን ሀብት ለማጋበስ በሚፈልጉት ሀገሮች አማካይነት ተረግጠው እያለቀሱ፣ በሥቃይና በዝምታ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሰዎች ይገኛሉ። በእነዚህ ጎስቋላ፣ ምስኪን፣ የቆሰሉ እና እግዚኣብሔር ከጎናቸው በሚቆምላቸው ሰዎች ስም ሆነንሰላማ በእዚያ ስፍራ ይሁን!” በማለት መማጸን ይኖርብናል።የመጽናናት አምላክ የሆነው” (2ቆሮ. 13) የተሰበረ ልብን የሚጠግን እና ሁሉንም ቁስል የሚፈውስ ጌታ ጸሎታችንን ይስማ።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.