2018-07-06 16:54:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ የዓለማችንን የአየር ንብረት ለውጥ ለመታደግ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በቀጣይነት መሥራት ይኖርብናል


ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ የዓለማችንን የአየር ንብረት ለውጥ ለመታደግ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በቀጣይነት መሥራት ይኖርብናል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ የዓለማችንን የአየር ንብረት ለውጥ ለመታደግ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በቀጣይነት መሥራት ይኖርብናል ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት በአሁኑ ወቅት በሮም ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው እና ቅዱስነታቸው የዛሬ ሦስት ዓመት ገደማ “Laudato si” በአማሪኛው “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁት ሐዋሪያዊ መልእክት ሦስተኛ አመቱን አስመልክቶ በመካሄድ ላይ ባለው ዓለማቀፍ ጉባሄ ላይ ተገኝተው ባደርጉት ንግግር እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን ይህ  ለሁለት ቀናት ያህል የተካሄደው ዓለማቀፍ ጉባሄ የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን እንከባከብ “የጋራ መኖሪያችንን እና የምድራችንን ሕይወት እንታደግ” በሚል መሪ ቃል ሲቃሄድ ቆይቶ በዛሬው እለት በተጠናቀቀው ጉባሄ ላይ ተገኝተው እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ ዓለማቀፍ ጉባሄ በቫቲካን በሚገኘው በክለመንቲና የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ መካሄዱን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚያው ተገኘተው ባደርጉት የመግቢያ ንግግር ለእዚህ ጉባሄ ተሳታፊዎች እንደ እንደ ገለጹት “እዚህ መገኘታችሁ ምድራችንን እና በምድራችን ላይ የሚገኘውን ሕይወት ለማዳን እና ለመታደግ ያላችሁን ቅርጥ ፈቃድ እና ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያላችሁን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ምልክት ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.