2018-06-21 09:47:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ፡ “የእኛን በር የሚያንኳኳ እያንዳንዱ እንግዳ ኢየሱስን ለመገናኘት እድሉ ይከፍትልናል”


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ፡ “የእኛን በር የሚያንኳኳ እያንዳንዱ እንግዳ ኢየሱስን ለመገናኘት እድሉ ይከፍትልናል”

በሰኔ 13/2010 ዓ.ም. በዓለማቀፍ ደረጃ የስደተኞች ቀን ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል።

የዓለም የስደተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አነሳሽነት የተመሰረተ የመታሰቢያ ቀን ሲሆን በእዚህም ቀን በዓለማችን የሚከሰቱትን ጦርነቶች እና ብጥብጦች ለሚሸሹ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦች ላይ የሚደርሰውን መከራ እና ስቃይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ለዓለም ለማሳወቅ በማሰብ የሚከበር በዓል ነው።

ተስፋ፣ መተማመን እና ወንድማማችነት የሚሉት ሦስት ቃላት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኃላ ስድተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ጉዳይ በተመለከተ በተደጋጋሚ የተናገሩዋቸው ቃላት እንደ ሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በሰኔ 13/2010 ዓ.ም  በመላው ዓለም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አነሳሽነት በዓለም ደረጃ የስደተኞች ቀን በመከበር ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በዓለም ደረጃ 66 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከገዛ ሀገራቸው በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ተፈናቅለው እንደ ሚኖሩ የሚታወቅ ሲሆን ይህ መፈናቀል የተከሰተው በጦርነት፣ በብጥብጥ፣ በተለያዩ ማኅበራዊ፣ ፖሌቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተነሳ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ካወጣው ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር ወር 07/2010 ዓ.ም ለእዚሁ ዓለማቀፍ የስደተኞች ቀን መዘጋጅ ይሆን ዘንድ በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት “የእኛን በር የሚያንኳኳ እያንዳንዱ እንግዳ ኢየሱስን ለመገናኘት እድሉ ይከፍትልናል” ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን “ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን መቀበል፣  መጠበቅ፣ ማብቃት እና ማዋሃድ" ያስፈልጋል በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው ቀደም ባሉ ጊዜያት ባደርጉት ስብከት እንደ ገለጹት በሮቻችንን እያንኳኩ የሚገኙ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ማስታወስ እና ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንደ ሚገባ በማውሳት  “ስደተኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ ከኢየሱስ ጋር የመገናኘትን አጋጣሚ እንደ ሚከፍት “ይህም ሁሉም ሊያውቀው እና ሊወጣው የሚገባው የመዳን ተግባር መገለጫ ነው ማለታቸውም ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በተደጋጋሚ ብዙ የዓለም ሀገራት ድንበሮቻቸውን ለስደተኞች ዝግ እያደርጉ መምጣታቸውን መገለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ብዙዎች ሀገራት ይህንን የሚያደርጉት ስደተኞ አንድ ጊዜ ወደ ሀገራቸው ከገቡ ተቀብሎ የሚያስተናግዳቸውን ሀገር ባሕል እና ማኅበራዊ ሁኔታ ተቀብለው ለመኖር ስለሚቸገሩ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች ቅዱስነታቸው መገልጻቸው የሚታወስ ሲሆን “ስደተኞችን ተቀብለው የሚያስተናግዱ ሀገራት ሕዝቦች “እነዚህ አዲስ የሚመጡ ሰዎች የነበረውን ማኅበራዊ መዋቅራችንን እና ልምዶቻችንን ያበላሻሉ የሚል ፍርሃት ስላላቸው መሆኑን ገልጸው፣ አንዳንዴም ባስ ሲል ሁሉም ሌቦች፣ እና ቀማኞች ናቸው የሚል እመንት በመያዛቸው የተነሳ፣ ያገሉዋቸዋል፣ የጸየፉዋቸዋል፣ ከሀገራቸውም እንዲወጡ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ያደርጋሉ ብለዋል።

“እነዚህ በሰብአዊ አዕምሮ ልንረዳው በምንችለው ጥርጣሬዎች ላይ የተመሠረቱ ናቸው። ጥርጣሬ እና ፍራሃት በራሱ ኃጢኣት አይደለም። ይህ ተግባር ኃጢኣት የሚሆነው ግን እነዚህ ጥርጣሬዎች እና ፍርሃቶች ለስደተኞች የምንሰጠው መልስ ላይ ተጽኖ ሲያደርጉ፣ እንዳንለግስ እጆቻችንን የሚይዙ ከሆነ፣ ጥላችን እና ክፋትን እንድናስብ ሲያደርጉን ነው”ማለታቸው ይታወሳል ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.