2018-05-30 19:12:00

ስለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፉ የሐሰት ዜናዎች” በሚል አርእስት አንድ መጽሐፍ ይፋ ሆነ


ስለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፉ የሐሰት ዜናዎች” በሚል አርእስት አንድ መጽሐፍ ይፋ ሆነ

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን መረጃን ለተጠቃሚዎች የሚያደርሱ በርካት የመገናኛ ብዙዕን አውታሮች እንዳሉ ይታወቃል። ልማዳዊ የሚባሉ የመረጃ መስጫ ተቋማት ለምሳሌም ከሬዲዮ እና ተሌቪዢን ባሻገር በሁኑ ወቅት መረጃን በትኩሱ ለተጠቃሚው የሚያደርሱ በእጅ ስልኮቻችን ላይ በምንጭናቸው የተለያዩ አፕሊኬሽኖች አማክይነት መረጃን በትኩሱ ማግኘት እንደ ሚቻችል ይታወቃል። በእዚህም ረገድ መረጃ ቀደም ሲል ባሉት ጊዜያት እንደ ለመድነው በአንድ ያጋዜጠኝነት ሙያ ባለው ሰው አማካይነት ብቻ የሚጠናቀር ዘገባ ብቻ ሳይሆን በእንግሊዘኛው “Citizen Juornalism” በአማሪኛው ዜጎች ከያሉበት ቦታ ሆነው የሚያገኙዋቸውን ትኩስ መረጃዎች የእጅ ስልኮቻቸውን በመጠቀም ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ባካተተ መልኩ  መረጃን ለተጠቃሚው በቃላሉ የሚያደርሱበት ጊዜ ላይ መድረሳችን በሚገባ ይታወቃል።

መረጃዎች ጠቃሚ የሆነ ይዞታ እንዳላቸው እሙን ቢሆንም ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ መልካቸውን በመቀየር ከጥላቻ ይሁን ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ እነዚህን ዘመናዊ የማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮችን በመጠቀም “fake News” የሐሰት ዜናዎች በከፍተኛ ሁኔታ እይተሰራጩ የግለሰብን፣ የሀገርን፣ የድርጅትን  ስም እና ገጽታ በማጉደፍ ላይ እንደ ሚገኙ፣ ይህም ተግባር በተለያዩ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ ጉዳዮ በሚመለከታቸው የማኅበርሰብ ክፍሎች ዘንድ ከፍተኛ ክትትል እይተደርገበት እርምት እየተወሰደበት የሚገኙ የአደባባይ ምስጢር ነው።

ይህንን በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 5/2010 ዓ.ም. የተከበረውን 52ኛው ዓለማቀፍ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ቀን አስመልክተው ከሬዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኛ አሌሳንድሮ ጂዞቲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደ ገለጹት የሰላም መንፈስ ማስፈን የሚችሉ ጋዜጠኞች ይበዙ ዘንድ በማበረታታት “ጋዜጠኞች ራሳቸው ሰው በመሆናቸው የተነሳ የጋዜጠኞ አገልግሎት ለሰው ልጅ መልካምነት እና ለሰላም መረጋገጥ” መሆን እንደ ሚገባው ገለጸው በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ውስጥ የሚኖሩ የማኅበርሰብ ክፍሎች ከጋዜዘጤኞች ሙያ ጋር በተያየዘ መልኩ ከፍተኛ የሆነ ተግዳሮት እየገጠማቸው እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

ከእዚህ ቀደም ይህ 52ኛው ዓለማቀፍ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ቀን በፈረንሳይ ሀገር በሚገኘው ሉርድ በሚባል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ጸበል በሚገኝበት የጸሎት ስፍራ የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ጳሮሊን በተገኙበት ተከብሮ ማለፉን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ በካርዲናል ፔትሮ ጳሮሊን አማካይነት በጥር 16/2010 ዓ.ም ባስተላለፉት የጽሑፍ መልእክት “እውነት ነጻ ያወጣችኃል” (ዩሐንስ 8፡32)“የውሸት ዜና እና ጋዜጠኛ ለሰላም” በሚል አርእስት ጠንካራ እና ሰፊ የሆነ መልእክት ለዓለም ማስተላላፋቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት መረጃ በብዙ መልኩ በጣም ጠቃሚ የሆነ ነገር ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን በእዚያው ልክ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ የሐሰት ዜናዎች እየተሰራጩ በመሆናቸው የተነሳ የመረጃ ጠጥቃሚ የሆነው የማኅበርሰብ ክፍል የመረጃ ምንጭ ለይቶ በማወቅ እውነት እና ሐሰት የሆነውን ዜና በመለየት ሂደት ውስጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

በቅርቡ ኔሎ ስካቮ እና ሮቤርቶ ቤሬታ በተባሉ ሁለት የጣሊያን ጋዜጠኞ የተጻፈ አንድ መጽሐፍ ለሕትመት መብቃቱ ይታወቃል። እነዚህ ሁለት ጣሊያናዊያን ጋዜጦች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በአምስት ዓመት የጵጵስና ዘመናቸው ስለእርሳቸው የተዘገቡትን የሐሰት ዜናዎች በማሰባሰብ እነዚህ ዜናዎች ሐሰት የሆኑ ዜናዎች መሆናቸውን ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ በመረጃ አስደግፈው ማቅረባቸው የታወቀ ሲሆን በእዚህም መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስክን በተመለከተ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ይፋ የሆኑ የሐሰት ዜናዎችን ማጋለጣቸው ታወቁዋል።

ይህ መጽሐፍ በእንግሊዘኛ ቋንቋ “Fake Pope፡ the false News on Pope Frances” በአማሪኛው  ስለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፉ የሐሰት ዜናዎች” በሚል አርእስት ልንባብ መብቃቱ የተገለጸ ሲሆን የእዚህ መጽሐፍ ደራሲ ከሆኑት ውስት አንዱ ጋዜጠኛ ኔሎ ስካቮ ሬዲዮ ከቫቲካን ጋር ባድረጉት ቆይታ እንደ ገለጹት የሐሰት ዜናዎችን በተመለከተ በርካታ መጽሀፍት ለንባብ መብቃታቸውን ገለጸው ከእነዚህ ለንባብ ከበቁት መጽሐፍት ውስጥ አብዛኞቹ የሐሰት ዜናዎችን እንዴት ለይተን ማወቅ እንደ ምንችል የሚያረዱ ማብራሪያዎች የተካተቱባቸው መሆናቸውን ገለጸው እነዚህን የሐሰት ዜናዎን ከተለያዩ ድኽረ ገጾች ላይ ማስወገድ የሚቻልበትን የምፍትሄ አቅጣጫ የሚያመላክቱ መጽሐፎች መሆናቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ላይ የሚቃጡትን የሐሰት ዜናዎችን በመቃወም የተጻፈ አንድም መጽሐፍ እንደ ሌለ የገለጹት ጋዜጠኛ ኔሎ እስካቮ በእዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮን አስመልክቶ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ የሚገኘውን የሐሰት ዜና መቋቋም እንዳልተቻለ ጨምረው ገልጸዋል። በእርግጥ የሐሰት ዜናዎችን የማሰራጨት ጉዳይ የተለመደ እና አዲስ የሆነ ነገር ባይሆንም ነገር ግን አሁን ከእዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በዓለም ደረጃ የመወያያ አርእስት እየሆነ የመጣ ጉዳይ እንደ ሆነ ገልጸው ይህም የሆነበት ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ያለውን ዘመን አመጣሽ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች እየተስፋፉ በመምጣታቸው እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

ይህ “Fake Pope፡ the false News on Pope Frances” በአማሪኛው  ስለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፉ የሐሰት ዜናዎች” የሚለውን መጽሐፍ ከጻፉት ጋዜጦኞች መካከል አንዱ የሆኑት ጋዜጠኛ ኔሎ ስካቮ ለሬዲዮ ቫቲካን ይህንን መጽሐፍ ለመጻፍ የተነሳሱበት ምክንያት አስምልክተው እንደ ተናገሩት ከአመታት በፊት “የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጠላቶች” በሚል አርእስት በታተመው መጽሀፍ ውስጥ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተግዳሮቶች እና እንቅፋቶች በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ እንደ ሆነ ገለጸዋል። “አሁን እኛ ለንባብ ባበቃነው መጸሐፍ ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮን በተመልከተ የተሰራጩ የሐሰት ዜናዎች ላይ ትኩረቱ” ያደርገ መጸሐፍ ለንባብ ማብቃታቸውን የገለጹት ጋዜጠና ኔሎ እስካቮ በተለይም ደግሞ ይህ “ስለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፉ የሐሰት ዜናዎች” በሚል አርእስት በቅርቡ በይፋ ለንባብ የቀረበው መጸሐፍ በተለያዩ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ውስጥ የተሰራጩ እና ሰለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተጻፉ የሐሰት ዜናዎችን ሐሰት መሆናቸውን በተጨባጭ በመረጃ በተደገፈ ሁኔታ ሀቁን ለእውነት ፈላጊ ማኅበርሰብ ያፋ ማድረግ እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮን የተመለከት በጣም በርካት የሐሰት ዜናዎች እንደ ሚገኙ የጠቀሱት ጋዜጠኛ ነሎ እስካቮ ነገር ግን እርሳቸው እና የስራ ባልደረባቸው ጋዜጠኛ ሮቤርቶ ባሬታ ባሳተሙት መጽሐፍ ውስጥ 80 ያህል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮን የተመለከቱ ቀንደኛ የሐሰት ዜናዎች የተካተቱ መሆናቸውን ገለጸው ማንም ሰው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮን በተመለከተ በተለያዩ የማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች አምካይነት የተሰራጩትን የሐሰት ዜናዎችን ለማረጋገጥ ከፈለገ ይህንን መጽሐፍት መመልከት እና እውነታውን ማረጋገጥ እንደ ሚቻል ጨምረው ገልጸዋል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.