2018-05-30 19:09:00

ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ክርስቶስን መቀበል እንችል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲቀባን ልንፈቅድለት ይገባል”።


ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮ  “ክርስቶስን መቀበል እንችል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲቀባን ልንፈቅድለት ይገባል”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።

በእዚህ መሰረት ባልፈው ሳምንት ማለትም በግንቦት 15/2010 ዓ.ም ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ ላይ ትኩረቱን ያደርገ እንደ ነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ምስጢረ ሜሮን “የምድር ጨው እና ብርሃን እንድንሆን ኃይልን የሚሰጠን መንፈስ ቅዱስን የምቀበልበት ምስጢር ነው” ማለታቸው መዘገባችን ይታወሳል።

በግንቦት 22/2010 ዓ.ም ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ ባልፈው ሳምንት  ከጀመሩት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ክርስቶስን በሚገባ መቀበል እንችል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲቀባን ልንፈቅድለት ይገባል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 22/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

ከእዚህ ቀደም በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ የጀመርነውን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህር በመቀጠል ዛሬ ደግሞ ይህ ምስጢር ክርስቲያንነትን የሚያስገኙ ምስጢራት ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር በመግለጽ ይፋ ለማድረግ እወዳለሁ።

የምስጢረ ጥምቀት ጸጋን የሚያረጋግጡ እና የሚያጠናክሩትን መንፈሳዊ የሆኑ ቅባ ቅዱሶችን ከመቀባቱ በፊት ምስጢረ መሮን ለመቀበል የተዘጋጁ እጩዎች በክርስትና አባታቸው እና በክርስትና እናታቸው አማካይነት በጥምቀታቸው ወቅት የገቡትን ቃል ኪዳን በድጋሚ እንዲያድሱ ይጠየቃሉ። አሁን እነሱ የቤተክርስቲያኗን እምነት ለመግለጽ ጳጳሱ ለሚያቀርብላቸው ጥያቄዎች "አምናለሁ" የሚል መልስ በመስጠት ዝግጁ ይሆናሉ። በተለይም "ጌታ የሆነው እና ሕይወት ሰጪ የሆነው መንፈስ ቅዱስ፣ በምስጢረ ሜሮን አማካይነት ልክ በጴንጤ ቆስጤ ቀን በሐዋሪያት ላይ እንደ ወረደ በእነርሱም ላይ የወርዳል።

የመንፈስ ቅዱስ ለመውረድ በጸሎት የተዘጋጀ ልብ ይፈልጋል፣ በእዚህም መልኩ የክርስቲያኑ ማኅበርሰቡ በጽሞና ጸሎት ካደርጉ በኃላ ጳጳሱ ምስጢረ ሜሮን ለመቀበል በተዘጋጀው እጩዎች ላይ እጁን በመጫንእግዚኣብሔር የእርሱን የሚያነጻወን አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱሱን በልጆቹ ላይ ያወርድ ዘንድ” ይማጸናል። መንፈስ ቅዱስ አንድ ነው፣ ነገር ግን በእኛ ላይ በሚወርድበት ወቅት ጥበብ፣ እውቀት ምክር፣ ጥንካሬ፣ እግዚአብሔርን መፍራት የተለያዩ ስጦታዎችን ይዞልን ይመጣል። መንፍስ ቅዱስ ይዞልን የሚመጣውን የስጦታ ዓይነቶች መጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ተጠቅሰው እንደ ሚገኙ እናውቃለን። እንደ ነቢዩ ኢሳያስ አገላለጽ በምስህ ላይ የወረዱት ሰባት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን እና እርሱ ተልዕኮውን በሚገባ እንዲወጣ የረዱትን ስጦታዎች ያመልክተናል እነዚህም  የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኀይል መንፈስ፣ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል በማለት ይገልጸዋል (ኢሳያስ 112) ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ   “መንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት” (ገላቲያ 522) በማለት ይገልጻቸዋል። አንድ የሆነው መንፈስ ቅዱስ  የተለያዩ ስጦታዎችን በመስጠት ቤተክርስቲያንን የሚያበለጽጉዋትን በርካታ ስጦታዎች ይሰጣል። የተለያዩ ነገሮችን የሚፈጥር ነገር ግን በተመሳሳይ መንገድ አንድ የሚያድርግ መንፍስ። መንፈስ ቅዱስ በተለያየ መንገድ እነዚህ ሁሉ ብልጽግናዎችን ይሰጠናል፣ በተመሳሳይም እነዚህ የተለያዩ ነገሮች ኅብረትን የመስርታሉ፣  ይህም እነዚህ ሁሉ መንፍሳዊ በረከቶች አንድ ክርስቲያን ያለው መንፈሳዊ ሀብቶች ናቸው።

በምስጢረ ጥምቀት ወቅት የተቀበልነው መንፈስ ቅዱስ ምስጢረ ሜሮንን በምንቀበልበት ወቅት በእጅ መጫን ስነ-ስረዓት ወቅት በጥምቀታችን ወቅት የተቀበልነው መንፍስ ቅዱስ ይረጋገጣል ማለት ነው። በጥንት ጊዜ የነበሩ ሐዋሪያት የክርስቶስን ፈቃድ ለመፈጸም እጆቻቸውን በመጫን የጥምቀትን ጸጋ የሚያሟላውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ለአዳዲስ ተጠማቂዎች ያስተላልፉ ነበር።

ቅባ ቅዱስ የሚሰጥበት ዘይት- ዘይት በሕክምናው ዘርፍ ሆነ በመዋቢያነት የሚንጠቀምበት ነገር እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን በተጎዳ ወይም በቆሰለ የአካል ክፍሎች ውስጥ በመግባት የማዳን ብቃት ያለው ንጥረ ነገሮች የተካተቱበት ነገር ነው። በእነዚህ ባሕርያት ምክንያት ዘይት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተምሳሌታዊ በሆነ መልኩ በመጠቀስ እና በስረዓተ አምልኮ ውስጥ ደግሞ በምስጢረ ጥምቀት ስነ-ስረዓት ወቅት በሚቀባው ቅባ ቅዱስ የሚቀድሰውን እና የሚያነጻውን የመንፈስ ቅዱስን ተግባር ያመለክታል። ምስጢረ ሜሮን በሚሰጥበት ወቅት ይህንን ምስጢር የቀበል ሰው በጳጳሱ አምካይነት እጁን በጭቅላቱ ላይ በመጫን እናየመንፈስ ቅዱስን ማሕተም ተቀበል፣ ይህንን ጸጋ የሰጠ እርሱ ቅዱስ ነውበሉ በመናገር ግንባሩን በቅባ ቅዱስ ይቀባል። መንፈስ ቅዱስ የማይታይ ጸጋ ነው፣ ነገር ግን በቅባ ቅዱስ አማካይነት በሚታይ መልኩ ይታተማል።

በእዚህ መልካም መዓዛ ባለው ቅባ ቅዱስ አማካይነት ምስጢረ ሜሮን የሚቀበለው ሰው ግንባሩን በሚቀባበት ወቅት የማይፋቅ መንፈሳዊ ምልክት በግንባሩ ላይ ይታተማል፣ ይህም ልዩ ባሕሪ እንዲጎናጸፍ በማድረግ ክርስቶስን እንዲመስል በማድረግ ይህንን ጸጋ በሰዎች መካከል በመልካም መዓዛ ለመልካም አገልግሎት ያውለዋል።

ምስጢረ ሜሮን በጥምቀት የተገኘውን ጸጋ ጥንካሬ እና ጥልቀት እንዲኖረው በማድረግ መንፈሳዊ ማሕተም እንድንታተም ያደርገናል፣ የተቀበልነውን ጸጋ ጠብቀን እንድንሄድ ያደርገናል። እግዚኣብሔር አባት መርጦ ምልክት አድርጎብናል፣ ከክርስቶስ ጋር በይበልጥ እንድንዋሐድ ያደርገናል፣የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች በይበልጥ በልባችን ጠብቀን እንድንሄድ ያደርገናል። መንፈስ ቅዱስ ተገቢ የሆነ ስጦታ በመሆኑ የተነሳ በምስጋና ልንቀበለው ይገባል፣ ለእርሱ ፈጣሪ ለሆነ ኃይል ቦታ ልንሰጥ ይገባል። በጥንቃቄ ልንጠብቀው የሚገባን ስጦታ ነው፣ በመልካም ሥራችን ልንደግፈው ይገባል፣ በእሳት በተሞላ ፍቅሩ ተደግፈን "ኢየሱስ ክርስቶስን በዚህ ዓለም ማንጸባረቅ" ይኖርብናል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.