2018-05-22 15:16:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለጣሊያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ አባላት “በሀገረ ስብከት ውስጥ ካህናትን መዋዋስ ያስፈልጋል”።


ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለጣሊያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ አባላት “በሀገረ ስብከት ውስጥ ካህናትን መዋዋስ ያስፈልጋል”።

በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 21/2010 ዓ.ም የጣሊያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ አመታዎ አጠቃላይ መደበኛ ጉባሄያቸውን መጀመራቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ አጠቃላይ መደበኛ ጉባሄ ላይ በጣሊያን ከሚገኙ የተለያዩ ሀገረ ስብከቶች የተውጣጡ ብጹዕን ጳጳሳት ተካፋዮች መሆናቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 13/2010 ዓ.ም በእዚሁ ጉባሄ ላይ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘተ ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በውቅቱ ባደረጉት ንግግር ላይ የጣሊያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄን በተመለከተ ሦስት ዋና ዋና የሚያስጨንቁዋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸው እነዚህም የወንጌላዊ ድኽነት መንፈስ እያነሰ በመምጣቱ የተነሳ ለመንፍሳዊ ጥሪ ምላሽ የሚሰጡ ወጣቶች ቁጥር መቀነስ፣ የኢኮኖሚ አስተዳደርን ለማሻሻል ግልጽነት መኖር እንደ ሚገባው እና በመጨረሻም ሀገረ ስብከቶችን ማጠናከር የሚሉት ሐሳቦች እንደ ሆኑ ለመረዳት ተችሉዋል።

በአንድ ሀገረ ስብከት ውስጥ የተሻለ ቁጥር ያላቸው ካህናት ካሉ እና በሌላው ሀገረ ስብከት ውስጥ ደግሞ ዝቅተኝ የሆነ ቁጥር ያላቸው ካህናት የሚገኙ ከሆ፣ ይህን ክፍተት ለመሙላት አንዱ ከአንዱ ጋር የሚረዳዳበትን መንገድ ማሰብ ይኖርባችኃል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የሀገረ ስብከቱን ገንዘብ እና መዋለነዋይ በማስተዳደር  ሂደት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ግልጽነት እንደ ሚያስፈልግ ጠቅሰው “ለአንድ ሰው የእራት ግብዣ ማድረግ ከፈለጋችሁ ከሀገረ ስብከቱ ገንዘብ ሳይሆን መጥቀም የሚገባችሁ ነገር ግን የገዛ ራሳችሁን የኪስ ገንዘብ ልትጠቀሙ ይገባል” ብለዋል። እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1964 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት የነበሩት ጳውሎስ ስድስተኛ በወቅቱ ጠይቀው እንደ ነበረ በጣሊያን የሚገኙትን ሀገረ ስብከቶች ቁጥር በመቀነስ ትናንሽ የሆኑ ሀገረ ስብከቶችን አንድ በማድረግ ማጠናከር እንደ ሚገብ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን ያልኩበት ምክንያት አሉ ቅዱስነታቸው  በትላንታንው  እለት የጣሊያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ አመታዎ አጠቃላይ መደበኛ ጉባሄ ላይ ባደርጉት ንግግር ይህንን “ያልኩበት ምክንያት እናንተን ለመውቀስ ፈልጌ ሳይሆን፣ ነገር ግን በጣም የሚያስጨንቀኝ ጉዳይ በመሆኑ የተነሳ እና ይህን በተመለከተ የተወሰኑ ቃላትን ለመናገር እና ለመውቀስ ጭምር ነው። ወቀሳ ደግሞ ኃጢኣት አይደለም” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት የጣሊያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ አጠቃላይ መደበኛ ጉባሄ ላይ ተገኝተው ባደርጉት ንግግር እራቸው “የሚይስጭነቀኝ ነገር” ካሉት ሦስት ነገሮች በቀዳሚነት የተቀመጠው መንፈሳዊ ጥሪን የተመለከተ ጉዳይ ሲሆን የጥሪን ጉዳይ በተመለከተ “በአንድ ወቅት ለብዙ መቶ አመታት ያህል ፍሬያማ፣ የወንጌል ልዑካን የሆኑትን ካህናት እና ደንጋላን፣ ገዳማዊያን/ገዳማዊያት ያለምንም ስስት ለዓለም ያበርክቱ የነበሩ ጣሊያንን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት እንደ ነበሩ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህ ሁኔታ አሁን ባለው የዓለማችን የባሕል ለውጥ እና ጊዜያዊ የሆኑ ነገሮችን ከመሻት፣ ገንዘብ አንባገነን እየሆነ በመምጣቱ የተነሳ ወጣቱ ሕይወቱን ለመንፈሳዊ ጥሪ እዳያውል እንቅፋት እየሆነ በመምጣቱ የተነሳ እንደ ሆነ ገልጸው በተጨማሪም አንዳንዴ በቤተክርስቲያን ውስጥ በፍጹም ሊከሰቱ በማይገባቸው ጉዳዮች ምክንያት እና ወንጌላዊ ምስክርነታችን ለብ ባለ መንፈስ በመዳረጋቸው የተነሳ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በእዚህም የተነሳ እየተከሰቱ የሚገኙትን የካህናት እጥረት ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ ብዙ ካህናት ያሉበት ሀገረ ስበክት የካህናት እጥረት ላለበት ሌላ ሀገረ ስብከት ካህናትን በመላክ ኅበረታቸውን ማጠናክር እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት የጣሊያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ አጠቃላይ መደበኛ ጉባሄ ላይ ተገኝተው ባደርጉት ንግግር እራቸው “የሚይስጭነቀኝ ነገር” በማለት ከዘረዘሩዋቸው ሦስት ነገሮች መካከል በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው ወንጌላዊ ድኽነት እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ግልጽነት ያስፈልጋል የሚለው ሐስብ እንደ ሆነ ቀድም ሲል መገለጻችን የሚታወቅ ሲሆን “እኔ የኢየሱሳዊ ማኅበር አባል እንደ መሆኔ “ለእኔ ወንጌላዊ ድኽነት የሐዋሪያዊ ሕይወት እናት እና ገድግዳ ነው፣ እናት የሆነበት ምክንያት ደግሞ ሐዋሪያዊ ሕይወታችን እንዲወለድ ስለሚያደርግ ነው፣ ግድግዳ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ ሐዋሪያዊ ሕይወታችን እንዳይሰናከል ስለሚጠብቀን ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። በእዚህም ምክንያት ወንጌላዊ የሆነ ድኽነት የሌለን ከሆነ ሐዋሪያዊ የሆነ ቅንዕት ወይም ወኔ በፍጹም ሊኖረን እንደ ማይችል የጠቀሱት ቅዱስነታቸው አንድ አማኝ የሆነ ሰው ስለድኽነት እየተናገረ፣ ነገር ግን በተጨባጭ እንደ ፈርሆን ሊኖር አይገባውም፣ ይህም በአንድ በኩል ስለ ወንጌላዊ ድኽነት ማውራት እና በሌላ በኩል ደግሞ የቅንጦት ወይም የተንደላቀቀ ሕይወት መኖር አይገባም፣ "የቤተክርስቲያንን ሙዕለ ንዋዮች እንደ ግልብ ንብረት አድርጎ ማስተዳደር በጣም አስቀያሚ የሆነ ነገር ነው" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንታንው እለት የጣሊያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ አጠቃላይ መደበኛ ጉባሄ ላይ ተገኝተው ባደርጉት ንግግር እራቸው “የሚይስጭነቀኝ ነገር” በማለት ከዘረዘሩዋቸው ሦስት ነገሮች መካከል ሦስተኛው እና የመጨረሻው በጣሊያን የሚገኙ ትናንሽ የሆኑ ሀገረ ስብከቶችን በአንድ ላይ በማድረግ ማጠናከር የገባል የሚለው እንደ ሆነ ቀድም ሲል መገለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ይህንን በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው “ይህ ጉዳይ ቀድም ባሉት ጊዜያ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር ከ1964 ዓ.ም  ጀምሮ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ጳውሎስ 6ኛ ጊዜ አንስቶ ሲጠና የነበረ ጉዳይ መሆኑን ቅዱስነታቸው ገልጸው የአከባቢውን መልካ ምድር፣ የሕዝቡን ባሕል፣ የካህናትን ቁጥር ከግምት ባስገባ መልኩ ታድሶ በማድረግ ትንንሽ የሆኑ ሀገረ ስብከቶች ተጣምረው አንድ ጠንክራ ሀገረ ስብከት የሚሆኑበት ሁኔታ እንዲፈጠር መስራት እንደ ሚገባ ቅድስነታቸው ጭምረው ከገለጹ በኃላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።  ይህ ጉባሄ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ካደርጉት ንግግር በመቀጠል በአሁኑ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እና  የጣሊያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ አበላት ብቻ በተገኙበት በዝግ በመካሄድ ላይ እንደ ሆነ ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።  
All the contents on this site are copyrighted ©.