2018-05-17 15:51:00

ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን ሞሃመድ በቫቲካን የኢትዮጲያ መንግሥት አንባሳደር ሆነው ተሾሙ


ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን ሞሃመድ በቫቲካን የኢትዮጲያ መንግሥት አንባሳደር ሆነው ተሾሙ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅድስት መንበር ልዑካን ሆነው የተመረጡ የተለያዩ ሀገራት አንባሳዳሮች የሹመት ደብዳቤ በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 09/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅሌሜንጦስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ መቀበላቸው ተገለጸ።

የእዚህን ዘገባ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ

እነዚህ የተለያዩ ሀገራት መንግሥታትን በመወከል በቫቲካን የቅድስት መነበር ልዑክ በመሆን የተሾሙት አንባሳድሮች የተውጣጡት ከታንዛኒያ፣ ከሌሴቶ፣ ከፓኪስታን፣ ከሞንጎሊያ፣ ከዴንማርክ፣ ከኢትዮጲያ እና ከፊንላንድ ሀገራት የተውጣጡ አንባሳድሮች እንደ ሆኑ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ የእነዚህን ሀገራት መንግሥታት የሚወክሉ አዲስ የተሾሙ አንባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ከተቀብሉ በኃላ ቅዱስነታቸው ባስሙት ንግግር እንደ ግለጹት በዓለማችን ውስጥ ፍትህ እና ስምምነት ለማስፋፋት ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ በታላቅ ትዕግሥት የሚሰራው ሥራ የእኛን ሰብአዊ የቤተሰብ አንድነት እና የእያንዳንዱን አባል ውስጣዊ ክብር ባማከለ መልኩ በጋራ እምነት ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው መጥቀሳቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ በቅድስት መንበር የተለያዩ ሀገራርት መንግሥታትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ ልዑካን የሹመት ደብዳቤ በቫቲካን በሚገኘው በቅልሜንጦስ የስብሰባ አዳራሽ በይፋ በተቀበሉበት ወቅት ያደርጉት ንግግር ትኩረርቱ አድርጎ የነበረው ሰላም፣ እርቅ፣ ስደተኞችን መቀበል እና መጠበቅ ይገባል በሚሉ ጭብጦች ዙሪያ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

በዓለማቀፍ ደረጃ የሚደረገው የዲምሎማሲ ግንኙነት በዓለማቀፍ ደረጃ ፍትህ እና ስምምነት እንዲፈጠር የሚያግዝ እንደ ሆነ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህም ሊከናወን የሚገባው  ሰብአዊ ቤተሰብ አንድነት እና የእያንዳንዱ አባላቱ ስብዕና ክብር ከግምት ባስገባ መልኩ ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በዚህ ምክንያት  የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ዋነኛው ዓላማ እያንዳንዱን ወንድ እና ሴት፣ ሕጻናት፣ አረጋዊያን ማዕከል ያደረገ ልማት መሆን እንደ ሚገባው ቤተክርስቲያን አጥብቃ እንደ ምታምን በግንኙነቱ ወቅት ባድርጉት ንግግር የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም በዓለማቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ውይይቶች እና ማዕቀፎች ማዳበር እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ከተደነገገ እነሆ ሰባ አመታትን እንዳስቆጠረ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን ድንጋጌ አሁንም በታደሰ መንፈስ ተግባርዊ በማድረግ  "ለሁሉም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በተለይም ደግሞ በድኽነት፣ በበሽታ እና በጭቆና ውስጥ ተዘፍቀው  እየተጎሳቆሉ ከሚገኙ ሰዎች ጋር አንድነትን በመፍጠር ከእዚህ ችግር ይላቀቁ ዘንድ የተቻለንን ሁሉ በማድረግ ተግባራዊ ማድረግ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ ደረጃ የግድዬለሽነት መንፈስ በከፍተኛ ደረጃ እየታየ እንደ ሚገኝ፣ አጣዳፊ ምላሽ የሚሻውን ኢፍታዊ የሆኑ ሁኔታዎችን የመቃወም እና የማጋለጥ ግበረ-ገባዊ ግድቴታችንን ማንም ቢሆን ችላ ሊለው የሚገባው ጉዳይ እንዳልሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በጣም አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየተከሰተ የሚገኘውን የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎችን ሁኔታ በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ በቅድስት መንበር የተለያዩ ሀገራት መንግሥታትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ ልዑካን የገዛ ሀገራቸውን አስገዳጅ በሆነ መልኩ በጦርነት እና በርሃብ እንዲሁም በተፈጥሮኣዊ ክስተቶች የተነሳ ከሀራቸው ተሰደው በክፍተኛ ድኽነት ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች በማገዝ ጥረት ውስጥ ተሳታፊ መሆን እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ጥሪ ማቅረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በቫቲካን የቅድስት መንበር የኢትዮጲያ መንግሥት አንባሳደር በመሆን የተሾሙት በአሁኑ ወቅት በፈረንሳይ የኢትዮጲያ መነገሥት አንባሳደር በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን ሞሃመድ እንደ ሆኑ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን ሞሃመድ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን ቆጣጠር በጥር 13/1953 ዓ.ም በኢትዮጲያ የተወለዱ እና እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1986 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ የሕግ ትምህርት ተከታትለው መመረቃቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በተጨማሪም ክቡር አንባሳደር አሊ ሱሊማን ሞሃመድ በኢትዮጲያ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ሀገራቸውን ማገልገላቸው የታወቀ ሲሆን በእዚህም መሰረት እ.አ.አ 1987-1994 የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ እ.አ.አ. 1994-1996 የአማራ ቢሔራዊ ክልል ጠቃላይ ፍርድበት ዳኛ፣ እ.አ.አ 1997-2001 የአማራ ብሔራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ እ.አ.አ 2001-2005 ዓ.ም የፍትህ ሚንስቴር ምክትል ሚንስቴር፣ እ.አ.አ ከ2005 ጀምሮ የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነር ኮሚሽነር እና የፀረ-ሙስና ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ በመሆን መገልገላቸውን ከቅድስት መንበር የዜና እና የሕትመት ቢሮ ካገኘነው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በፈረንሳይ የኢትዮጲያ መንግሥት አንባሳደር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፣ በተመሳሳይ መልኩም ቫቲካን የኢትዮጲያ መንግሥት አንባሳደር በመሆን ከዛሬ ከግንቦት 09/2010 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ አገልግሎታቸውን መጀመራቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.