2018-05-11 10:47:00

የክርስቶስን አብነት በመከተል በፍቅር እና በአንድነት ኑሩ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 02/2010 ዓ.ም ከሃያዎቹ ጣሊያን አውራጃዎች ውስጥ ሁለቱን ማለትም የግሮሴቶ አውራጃ ውስጥ በሚገኘው የግሮሴቶ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ኖማዴልፊያ የተሰኘችውን ትንሽ ከተማ እና  የፍሎሬንስ አዋራጃ ውስጥ የሚትገኘውን የፊዞሌ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ሎፒያኖ የምትባል ከተማ ተገኝተው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 02/2010 ዓ.ም ያደረጉትን ሐዋሪያዊ ጉብኝት የጀመሩት በግሮሴቶ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ኖማዴልፊያ የተሰኘችውን ትንሽ ከተማ በመጎብኘት እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻ ሲሆን በእዚህች በኖማዴልፊያ በመባል በምትታወቀው ትንሽዬ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ማኅበርሰብ የተመስረተው እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1947 ዓ.ም. በአንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህን በነበሩት በክቡር አባ ዜኖ ሳልቲኒ በታባሉ ካህን እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእዚያ ከሚገኙ የማኅበርሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን በግንኙነቱ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባድረጉትን ንግግር እንደ ገለጹት የእዚህ ማኅበርሰብ መስራች የሆኑት ክቡር አባ ዜኖ ሳልቲን ይህንን ማኅበርሰብ ከመመስረታቸው በፊት በታላቅ ሐዋሪያዊ ስሜት እና ፍላጎት ይህ ማኅበርሰብ የወንጌልን ዘር ተቀብሎ ፍሬያማ ማድረግ የሚችልበትን ምቹ ሁኔታዎች በቅድሚያ አመቻችተው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው መግለጻቸው የታወቀ ሲሆን ይህ የተዘራው የወንጌል ዘር ፍሬያማ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጾ አብርከተው ማለፋቸውን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

የእናንተ የአኗኗር ሁኔታ በሚገባ የሚገለጸው የወንድማማችነት ባሕሪይ የእዚህ ማኅበርሰበ መስራች የነበሩ የአባ ዜኖ ሕልም እና ግብ የነበረ ሲሆን እርሳቸው በሕይወት ዘመናቸው በጥንት ጊዜ በሐዋሪያት ሥራ ውስጥ የተጠቀሱትን ዓይነት የማኅበረሰብ ክፍሎችን የመሰል ማኅበረሰብ ለመመስረት ምኞቱ ነበራቸው። ይህንን በተመለከተ እንዲህ ይሉ ነበር “አማኝ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በሙሉ አንድ ልብ እና አንድ መንፈስ ነበራቸው፣ ከእነርሱ መካከል ማንም ሰው የግሉ የሆነ ንብረት እንዳለው አድርጎ አይቆጥርም ነበር፣ የነበራቸው ነገሮች ሁሉ የጋራ ነበር” በማለት ይናገሩ ነበር። በቅዱስ ወንጌል እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመተማመን፣ ክርስቲያናዊ ምስክርነትን በእዚሁ መልክ በመስጠት የእዚህ ዓይነቱን ሕይወት መኖር እንድትቀጥሉ አደራ እላለሁ።

የኖማዴልፊያ ማኅበርሰብ መስራች ክቡር አባ ዜኖ ሳልቲኒ ማንንም ሰው ያላገለለ፣ ሁሉም ሰዎች በፍቅር ተሳስበው የሚኖሩበት ማኅበርሰብ ለመመስረት መብቃታቸው በጣም የሚያስደንቅ መሆኑን በሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው ወቅት የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አባ ዜኖ ማንም ሰው ያላገለለ ሁሉንም ሰው አቅፎ የያዘ ማኅበርሰብ በወቅቱ መመስረታቸው የሚያስደንቅ ተግባር እንደ ሆነ ገልጸው በተለያዩ ቤተሰቦች ውስጥ እምነትን ማዕከል ባደርገ መልኩ ትብብር እና ትስስርን በመፍጠር ሁሉም የማኅበርሰቡ አባል እንደ ወንድም እና እህት በመግባባት የሚኖሩበት ማኅበርሰብ መፍጠራቸው ታላቅ የሆን ተግባር እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በእዚህም መልኩ አባ ዜኖ የመሰረቱት ኖማዴልፊያ ማኅበርሰብ ጌታ ለሚያቀርብልን ልዩ ጥሪ ምላሽ መስጠታቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንንም በእዚህ ማኅበርሰብ ውስጥ በሚኖሩ በእያንዳንዱ ገለሰብ ውስጥ ጠንካራ የሆነ ትስስር እንዲኖር በማድረግ ለጌታ ጥሪ ምላሽ መስጠታቸውን ገልጸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሚለን ከውሃ እና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም መወለድ ያስፈልጋል እንዳለው ሁሉ “የእግዚኣብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ሁሉ እርሱ የእኔ ወንድም፣ እህት እና እንዲሁም እናት ነው” ያለውን የኢየሱስን ቃል በማስታወስ በሕብረት እና በአንድነት በምንኖርበት ሥፍራ ሁሉ ፍቅር ይኖራል፣ ፍቅር ባለበት ቦታ ደግሞ እግዚኣብሔር በእዚያ ይኖራል፣ በእዚህም ምክንያት ሕበረታችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉ በማለት ቅዱስነታቸው መናግራቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.