2018-05-11 15:24:00

የመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብል ውስጥ የተቀሰቀሰው ጦርነት ያፋፋመው ሕገወጥ የወርቅ እና የአልማዝ ሽያጭ መሆኑ ተገለጸ።


የመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብል ውስጥ የተቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ጦርነት ያፋፋመው ሕገወጥ የወርቅ እና የአልማዝ ሽያጭ መሆኑ ተገለጸ።

በአሁኑ ወቅት የመካከለኛ አፍሪካ ሪፖብልክ በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ እንደ ምትገኝ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን በተመለከተ በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት በእዚህች የመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብል ውስጥ የተቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ጦርነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀጣጠል ያደርገው ሕገወጥ የወርቅ እና የአልማዝ መአድናት ዝውውር እና ሽያጭ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ገለጸዋል

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጭወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባለፈው እሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰብሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎ በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደርጉ በኃላ እንደ ተለመደው ዘወትር እሁድ እለት ለዓለም በሚያስተላፉት መልእክት እንደ ገለጹት “እኔ ራሴ በአካል ተገኝቼ ለመጎብኘት እድል ባገኘውባት እና ሁልጊዜም ቢሆን በልቤ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ቦታ ባላት በእዚህች የመከከለኛው አፍሪካ ሪፖብልክ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በአዲስ መልክ በተቀሰቀሰው ግጭት የተነሳ ካህናት የሚገኙበት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ያወሱት ቅዱስነታቸው በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብልክ ሰላም ይፈጠር ዘንድ ልንጸልይ የገባል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከታኅሳስ 01/2008 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 11/2009 ዓ.ም. ደርስ ለ349 ቀናት ያህል የቆዬ ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ኢዩቤልዩ አውጀው የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን ልዩ ቅድሱ የምሕረት ዓመት በወቅቱ በክርስቲያኖች እና በሙስሊም እምነት ተከታዮች መካከል በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በተነሳው እርስ በእርስ ግጭት ተጎሳቁላ በነበረች ሀገር ዋና ከተማ ባንጉይ በመገኘት የሁለቱንም የሐይማኖት ተወካዮች በአንድነት ፊት ለፊት አቀራርበው በማናጋገር እርቅ እንዲፈጥሩ መነገዱን በመክፈት በእዚያው በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብልክ በባንጉዊ ከተማ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል ተገኝተው ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ኢዩቤሊዪን ማስጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን በእነዚህም 349 ቀናት ውስጥ ምዕመናን  መንፈሳዊ እና አካላዊ የምሕረት ተግባራት የሚፈጸሙበት ወቅት መሆኑን ገልጸው፣ በእዚህ ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ክርስቲያኖች እርቅን እና ሰላምን ይፈጥሩ ዘንድ ማሳሰባቸው ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.