2018-05-11 15:31:00

በደቡብ ሱዳን 200 ሕጻናት ወታደሮች ነጻ መሆናቸው ተገለጸ


በደቡብ ሱዳን 200 ሕጻናት ወታደሮች ነጻ መሆናቸው ተገለጸ

ደቡብ ሱዳን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2011 ዓ.ም ነጻነቱዋን በመቀናጀት የዓለማችን  195ኛው ሀገር በመሆን መቀላቀሏ ይታወሳል። ደቡብ ሱዳን ነጻነቱዋን ከተቀናጀችበት የጎርጎሮሳዊያኑ የ2011 ዓ.ም. ጀምሮ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳልተለያት የሚታወቅ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በእዚህች የዓለማችን አዲስ ሀገር ውስጥ ሰላም እና እርቅ በማምጣት ዜጎቹዋ ከስቃይ እና ከጦርነት ለመትዳግ የተደርጉ ጥረቶች በሙሉ በተለያዩ ምክንያቶች መክሸፋቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም የተነሳ ለከፍተኛ የእርስ በእርስ ጦርነት መጋልጧ ይታወቃል። በእዚህ የእርስ በእርስ ጦርነት ተሳታፊ የሆነ ለአቅመ ሄዋን እና ለአቅመ አዳም ያልደርሱ በርካታ ሕጻናት በስገዳጅ ሁኔታ የውትድርና አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህ በርካታ እጻናት ወታደሮች ውስጥ በቅርቡ 200 የሚሆኑቱ ነጻ መውጣታቸው እና ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የተገልጸ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 95 ሴቶች እንደ ሆኑ ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጭወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ከእነዚህ ነጻ ከወጡ ሕጻንት ወታድሮች መክከል አንዳንዶቹ እንደ ገለጹት የወትድርና አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በተለያየ ዓይነት ወንጀሎች ውስጥ መሳተፋቸው መናገራቸው የተገልጸ ሲሆን በእዚህ የሕጻንነት እድሜያቸው የውትድርና አገልግሎት ውስጥ እንዲሳተፉ ያደርጋቸው ነገሮች መካከል በጣም ብዙ ብር እየተከፈላቸው እንደ ሚማሩ ቃል ስለተገባላቸው እንደ ሆነ ጠቅሰው ነገር ግን ይህ ቃል የተገባላቸው ገንዘብ እና የትምህርት እድል እንድልተሰጣቸው በሀግሪቷ ለሚገኘው የካቶሊክ ሚዲያ ኔት ወርክ መገለጻቸው ታውቁዋል። በቅርቡ የምስራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ብጽዕን ጳጳሳት ጉባሄ ምክር ቤት ባወጣው መገለጫ እንደ ገለጸው በደቡብ ሱዳን የትጥቅ ትግል ውስጥ የተሳተፉ አካላት በሙሉ ከእዚህ አሰቃቂ እና አውዳሚ ከሆነው ጦርነት ተላቀው ለሀግራቸው ሰላም፣ እድገት እና መረጋጋት የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

እነዚህ በቅርቡ  ከውትድርና አገልግሎት ነጻ በመሆን የተለቀቁ ሕጻንት አስፈላጊ የሆነ የሕክምና ምርመራ ከተደርገላቸው እና አንዳንድ ስልጠናዎች ከተሰጣቸው በኃላ ወደ መደበኛ ትምህርታቸው እንደ ሚመለሱ መገለጹን የቫቲካን የዜና ምንጭ የሆነው ፌዴስ ካወጣው ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.