2018-05-09 15:22:00

ቅድስት መንበር ምዕመናንን፣ ቤተሰብን እና ሕይወትን በተመለከተ አዲስ ውስጠ ደንብ ማውጣቱዋ ተገለጽ።


ቅድስት መንበር ምዕመናንን፣ ቤተሰብን እና ሕይወትን በተመለከተ አዲስ ውስጠ ደንብ ማውጣቱዋ ተገለጽ። በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አነሳሽነት እና በቅድስት መነበር ሥር የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅርብ የሐዋሪያዊ ሥራዎች የመማክርት ጉባሄ አባላት በጋር በመሆን ምዕመናን እና ቤተሰብ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ በማሰብ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2016 ዓ.ም ልዩ ልዩ ተግባራትን በማከናውን ላይ እንደ ነበረ የሚታወቅ ሲሆን ይህ የቅዱስነታቸው የሐዋሪያዊ ሥራዎች  የቅርብ የመማክርት ጉባሄ አባላት ምዕመኑን፣ ቤተሰብን እና ሕይወትን የተመለክቱ ጉዳዮችን በጥልቀት በማንሳት በቤተክርስቲያን ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባን ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ ከገመገመ በኃላ ያወጣው ቤተክርስቲያኗ የምትተዳደርበት ውስጠ ደንብ መሆኑን ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ በዛሬው በግንቦት 01/2010 ዓ.ም. ይፋ የተደረገው ምዕመናንን፣ ቤተሰብን እና ሕይወትን የተመለከተ  የቤተክርስቲያኒቷ ውስጠ ደንብ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሐምሌ 15/2016 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በራሳቸው አነሳሽነት በላቲን ቋንቋ motu Proprio Sadula Mater በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም በሥራ የተጠመደች እናት በሚል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አነሳሽነት የምዕመናን ምክር ቤት የተሳተፉበት፣ በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው የቤተሰብ ጉዳይን የሚከታተለው ምክር ቤት እንዲሁም አሁንም በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው እና ሰለሕይወት ጥናት የሚያደርገው ጳጳሳዊው የቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛ ኢንስቲቱት ተካፍይ የሆኑበት እና በጋር ባደርጉት ጥረት ለውጤት የበቃ የቤተክርስቲያኗ ውስጠ ደንብ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

 ይህ ውስጠ ደንብ ምዕመኑ በግለሰብ እና በማኅበር ደረጃ በቤተክርስቲያን እና በዓለም ውስጥ ሳይቀር ያላቸውን የክርስትና ተልዕኮ እንዴት መወጣት እንደ ሚችሉ የሚገልጹ አንቀጾች የሚገኙበት እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በገለሰብ ደረጃ እያንዳንዱ ምዕመን በሚኖርበት እና በሚሠራበት ቦታ ሁሉ ሳይቀር በአጠቃላይ በመላው ሕይወቱ የክርስትና እሴቶችን መመስከር እንደ ሚኖርበት የሚመክር ነው። በማኅበር ደረጃ ደግሞ እያንዳንዱ ምዕመናን በማኅበር በመደራጀት ወይም ደግም የተለያዩ ዓይነት ንቅናቄዎችን በመፍጠር ምስጢረ ጥምቀትን በተቀበሉበት ወቅት የተቀበሉትን ሐዋሪያዊ ኃላፊነት በግለሰብ እና በማኅበር ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ መጣር እንደ ሚጠቅባቸው የመገልጽ ውስተ ደንብ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በቤተክርስቲያን ሕይወት እና ተልዕኮ ውስጥ በንቃት በመሳተፍ እያንዳንዱ ምዕመን በተቀበለው መክሊት ላይ ተመስርቶ ለማኅበርሰብ እድገት እና ሕነጻ የበኩላቸውን አዎንታዊ ተግባር እንዲያበረክቱ ከፍተኛ ግንዛቤ የሚሰጥ ውስጠ ደንብ ነው።

ወጣቶችን በተመለከተ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ወጣቶች በዓለማችን ውስጥ እያጋጠማቸው ያለውን በርካታ ተግዳሮቶችን በመጋፈጥ በቤተክርስቲያን ተልዕኮ ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋጾ ማድረግ እንደ ሚኖርባቸው ግንዛቤ የሚፈጥር ውስጠ ደንብ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

ቤተሰብን በተመለከተ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ግንዛቤዎች እንዲፈጠሩ እና ለቤተሰብ የሚደረገው ሐዋሪያዊ እንክብካቤ እና የቤተሰብን መብቶች በተመለከተ ሰፋ ያለ ምክሮች እና ደንቦች የሚገኙበት ውስጠ ደንብ እንደ ሆነም ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተለይም ደግሞ በምስጢረ ተክሊል ላይ መስረቱን ያደረገ ሐዋሪያዊ አስተምህሮ በተከታታይ በቤተሰብ ደረጃ መሰጠት እንዳለበት፣ ቤተሰብ ቀጥይነት ባለው መልኩ ሐዋሪያዊ የሆነ እንክብካቤ ሊደርግለት እንደ ሚገባ፣በእዚህ ረገድ ቤተሰብ ቤተክርስቲያን ውስጥ እና በማኅበርሰቡ ውስጥ ሳይቀር ያለውን መብት እና ግዴታ  በመጥቀስ በቤተሰብ ውስጥ ሆነ በማኅበርሰቡ ውስጥ የሚነሱ ችግሮችን በውይይት መንፈስ ብቻ መፈታት እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚሰጥ ውስጠ ደንብ መሆኑን ለመረዳት ተችሉዋል።

ሕይወትን በተመለከተ ደግም በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በተለያየ ዓይነት የመድብለ ዘር ምህንድስና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከሕይወት ጋር በተያያዘ መልኩ በጣም በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ እንደ ሚገኙ የሚያወሳ ውስተ ደንብ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የስነ-ምግባር አንቀጸ-ሕግ ላይ መስረቱን ባደረገ መልኩ የመድብለ ዘር ምህንድስና ቴክኖሎጂ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ሊያስከትለው የሚችለውን መስረታዊ ችግር ቀጣይነ ባለው መልኩ በማጥናት ለሰው ልጆች ሕይወት ክብር እንዲሰጥ እና እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የሰው ልጅ ሕይወትን በተመለከተ በከፍተኛ ኣሁኔታ እይተንሰራፋ የመጣውን አሉታዊ የሆነ ርዕዮተ ዓለማዊ አስተሳስብ በአግባቡ ምልሽ ለምሰጠት የሰው ልጆች ሕይወት ሰብዕዊ ክብሩ ተጠብቆ እንዲቀጥል ማድረግ የሚችሉ ሁኔታዎችን በስፋት የሚገኝበት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጣዊ ሕገ ደንብ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አነሳሽነት እና በቅድስት መንበር ሥር የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅርብ የሐዋሪያዊ ሥርዎች የመማክርት ጉባሄ አባልት ጋር በጋር በመሆን  የተዘጋጀው ምዕመናን እና ቤተሰብ በቤተክርስቲያ እና በዓለም ውስጥ ሊኖራቸው ስለሚገባ ተልዕኮ እንዲሁም በተጨማሪም የሰው ልጆች ሕይወት ክቡር መሆኑን የሚገልጸው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጠ ደንብ በመጪው እሁድ በግንቦት 5/2010 ዓ.ም የፋጢማ የምቁጠሪያይቱ ማሪያም አመታዊ ክብረ በዓል በሚከበርበት ወቅት ለንባብ እንደ ሚበቃ ለመረዳት ተችሉዋል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.