2018-05-08 15:47:00

ዓለማቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር በዓለማቀፍ ደረጃ 17 ሚልዮን የበጎ ሥራ አባልት እንዳሉት ተገለጸ።


ዓለማቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር በዓለማቀፍ ደረጃ 17 ሚልዮን የበጎ ሥራ አባልት እንዳሉት ተገለጸ።

በዛሬው እለት ማለትም በሚያዝያ 30/2010 ዓ.ም. ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ቀን ተከብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ቀን በዛሬው እለት ረፋዱ ላይ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ በርካታ የጣሊያን የቀይ መስቀል ማኅበር አባላት በተገኙበት መከበሩ ተገልጹዋል። በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኘው ለጣሊያን የቀይ መስቀል ማኅበር አባላት ንግግር ማድረጋቸውን ለመረዳት ተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው ባለፈው ጥር 16/2010 ዓ.ም ከጣሊያን የቀይ መስቀል ማኅበር አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት የእናንተ ተግባር በመፍሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከተጠቀሰው የደጉ ሳምራዊ ተግባር ጋር ይመሳሰላል” ማለታቸውን መዘግባችን ይታወሳል።

ላለፉት 150 ዓመታት ያህል በሚያዝያ 30 ቀን ይህ ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ማኅበር ቀን እና ዓለማቀፍ የቀይ ጨረቃ ማኅበር እንደ ሚከበር የሚታወቅ ሲሆን ይህ በዓለ በእዚህ ቀን የሚከበረው የዛሬ 150 ዓመት ገደማ እነዚህን ሁለት ማኅበራት በመሰረተው እና ሰብዕዊ አገልግሎቶችን በሕይወቱ ዘመን አከናውኖ ባለፈው ሲውዘርላንዳዊው ሄንሪ ዱናንት የልደት ቀን የሚከበር ዓለማቀፋዊ በዓለ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

የቀይ መስቀል ማኅበር በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ ደረጃ 17 ሚልዮን የቦጎ ሥራ አባልት ያሉት ማኅበር እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን በዋነኛነት “አነስተኛ የሆኑ ልምዶችን በመጠቀም ሕይወትን እንዴት ማዳን ይቻላል?" የሚለውን አመለካከት በዘጎች ውስጥ በማስረጽ ድነገተኛ የሆኑ አደርጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ሁሉ ዜጎች ባላቸው ችሎታ እና አቅም የአደጋ ሰላባ የሆኑትን የማኅበርሰብ ክፍሎችን እንዴት ማገዝ እንደ ሚችሉ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ በተለይም ደግሞ ድንገተኛ የሆኑ ማንኛቸውም ዓይነት አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ለተጎችጂው ሰው የመጀመሪያ እርዳታ የሚሰጡበትን ክህሎት እንዲያዳብሩ የሚረዳ ዓለማቀፍ ማኅበር ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት የተከበረውን ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ቀን በማስመልከት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ የስብሰባ አዳራሽ ከጣሊያን የቀይ መስቀል ማኅበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት እንደ ገለጹት "አንድ የበጎ ፈቃድ ማኅበር ዋንኛው ተልዕኮ መሆን የሚገባው  እርዳታ ፈላጊ ለሆነ አንድ ሰው የሚያስፈልገውን እርዳታ ፍቅር በተሞላው መልኩ በነጻነት መስጠት መሆን እንደ ሚገባው” ገልጸው በአጠቃላይ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን የደጉ ሳምሪዊ ተግባር ማከናወን መሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸው የተጎጂውን ሰው ሥነ-ምግባራዊ ባሕሪይ ወይም ያለውን ሀይማኖት ጥያቄ ውስጥ ሳናስገባ በተቻለን አቅም እና ፍጥነት ቁስሎቹን ማዳን እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ዓለማቀፍ የቀይ መስቀል ማሕበር ሰብኣዊ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ የተባሉ  ሦስት መርሆች ያለው ዓለማቀፍ ማኅበር እንደ ሆነ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ለምሳሌም በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በተፈጥሮ አደጋዎች እና ባህር ላይ አደጋ የሚያጋጥማቸውን ስደተኞ ሳይቀር ለመርዳት በዓለማቀፍ ደረጃ እነዚህን በጎ ተግባራት በማስተባበር የእርዳታ ስራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማቀናጀት ዋነኛው ተግባራቸው ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው በአክብሮት መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.